ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- መጋቢት:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሚያዝያና ግንቦት:- መጽሔቶች፤ ሰኔ:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
◼ ጉባኤዎች አዳዲስ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት እትሞች እንደደረሷቸው ለአስፋፊዎች መስጠት ይኖርባቸዋል። እንዲህ ማድረጋቸው አስፋፊዎች መጽሔቶቹን ከማበርከታቸው በፊት እንዲያነቧቸው ያስችላቸዋል።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የወከለው አንድ ወንድም የታኅሣሥን፣ የጥርንና የየካቲትን የጉባኤ ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። ሒሳቡን አንድ ሰው ብቻ በተከታታይ መመርመር አይኖርበትም። የሒሳብ ምርመራው ውጤት የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ለጉባኤው መነበብ አለበት።—ለጉባኤ ሒሳብ አያያዝ የወጣ መመሪያ (S-27) የሚለውን ተመልከት።
◼ በ2008 የምናደርገው የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም የሚከተለው ነው:-
ጥቅ. 3-5 አዲስ አበባ አማርኛ
ጥቅ. 10-12 አዲስ አበባ አማርኛ/ የምልክት ቋንቋ
ድሬዳዋ አማርኛ
ነቀምቴ አማርኛ
ሶዶ አማርኛ
ጥቅ. 17-19 አዲስ አበባ አማርኛ
ደሴ አማርኛ
ጊምቢ ኦሮምኛ
ናዝሬት አማርኛ
ይርጋለም ሲዳምኛ
ጥቅ. 24-26 አዲስ አበባ አማርኛ/ እንግሊዝኛ
አለታ ወንዶ አማርኛ
አምቦ ኦሮምኛ
ሻሸመኔ አማርኛ
ጥቅ. 31-ኅዳር 2 አዲስ አበባ አማርኛ
ባሕር ዳር አማርኛ
ጅማ አማርኛ
መቀሌ ትግርኛ
ሶዶ ወላይትኛ
◼ የ2008 የአውራጃ ስብሰባ ጭብጥ “በአምላክ መንፈስ መመራት” የሚል ነው። በሦስቱም ቀን ስብሰባ ላይ ለመገኘት ፕሮግራማችሁን ማስተካከል እንድትችሉ ጠቃሚ የሆኑ ዝርዝር መረጃዎች ወደፊት በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ይወጣሉ። በሦስቱም ቀን ስብሰባ ላይ ለመገኘት አሠሪያችሁን ፈቃድ መጠየቅ የምትፈልጉ ከሆነ እንዲህ ከማድረግ ወደኋላ አትበሉ።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- እንግሊዝኛ:- እስከ ምድር ዳር ድረስ/መለኮታዊ ትምህርት በዲቪዲ፤ ፈረንሳይኛ:- ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር 2008፤ ትግርኛ:- በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- ፈረንሳይኛ:- ማመራመር፣ የወጣቶች ጥያቄ፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ የአምላክ ወዳጅ፣ ሮድ ቱ ኤቨርላስቲንግ ላይፍ፤ ኦሮምኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ ስፓንኛ:- የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ ትግርኛ:- ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ራእይ።