የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 4/08 ገጽ 3
  • ‘የእሱን ፈለግ ተከተሉ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የእሱን ፈለግ ተከተሉ’
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው”
    “ተከታዬ ሁን”
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ‘መጥተህ ተከታዬ ሁን’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • በፍቅር በማስተማር ኢየሱስን ምሰሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 4/08 ገጽ 3

‘የእሱን ፈለግ ተከተሉ’

1. ውጤታማ አገልጋዮች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

1 ኢየሱስ፣ የረቢዎች ትምህርት ቤት ገብቶ ባይማርም በታሪክ ዘመናት ሁሉ ከኖሩት የሚበልጥ ታላቅ የወንጌል ሰባኪ ነው። ደስ የሚለው ነገር፣ ኢየሱስ ያከናወነው የወንጌል አገልግሎት ለጥቅማችን ሲባል በጽሑፍ መስፈሩ ነው። ውጤታማ አገልጋዮች መሆን እንድንችል ‘የእሱን ፈለግ መከተል’ ይገባናል።—1 ጴጥ. 2:21

2. ኢየሱስ ለሰዎች የነበረውን ዓይነት ፍቅር ለማዳበር ምን ሊረዳን ይችላል?

2 ለሰዎች ፍቅር አሳዩ:- ኢየሱስ አገልግሎቱን ለመፈጸም ያነሳሳው ለሰዎች የነበረው ፍቅራዊ አሳቢነት ነው። (ማር. 6:30-34) በክልላችን የሚገኙ ብዙ ሰዎች “በመቃተት” ላይ ስለሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማወቅ በጣም ያስፈልጋቸዋል። (ሮሜ 8:22) እነዚህ ሰዎች ያሉበትን አሳዛኝ ሁኔታ ስንመለከት እንዲሁም ይሖዋ ለእነሱ ያለውን ፍቅራዊ አሳቢነት ስናስብ በስብከቱ ሥራ ወደፊት ለመግፋት እንነሳሳለን። (2 ጴጥ. 3:9) ከዚህም በተጨማሪ ሰዎች ከልብ እንደምናስብላቸው ከተረዱ ለመልእክታችን ፈጣን ምላሽ ይሰጣሉ።

3. ኢየሱስ ለሌሎች ለመስበክ ምን ምን አጋጣሚዎችን ተጠቅሟል?

3 ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ተናገሩ:- ኢየሱስ ምሥራቹን ለሌሎች ለማካፈል ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅሟል። (ማቴ. 4:23፤ 9:9፤ ዮሐ. 4:7-10) እኛም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችንን ስናከናውን እውነትን ለሌሎች ለመናገር የተዘጋጀን መሆን ይገባናል። አንዳንዶች በሥራ ቦታና በትምህርት ቤት አልፎ ተርፎም ጉዞ ሲያደርጉ፣ ገበያ ሲወጡና በሌሎች ጊዜያት ለመመሥከር እንዲያመቻቸው መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ጽሑፎች ይይዛሉ።

4. የስብከታችን ጭብጥ የአምላክ መንግሥት እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

4 በመንግሥቱ ላይ አተኩሩ:- የኢየሱስ የስብከት ጭብጥ የመንግሥቱ ወንጌል ነበር። (ሉቃስ 4:43) ምንም እንኳ መግቢያችን በቀጥታ ስለ መንግሥቱ የሚጠቅስ ባይሆንም የምናነጋግረው ሰው የአምላክን መንግሥት አስፈላጊነት እንዲገነዘብ መርዳት እንዳለብን መዘንጋት አይኖርብንም። በመጨረሻው ዘመን እንደምንኖር የሚጠቁሙትን በዓለም ላይ የሚታዩ መጥፎ ሁኔታዎችን አንስተን በምንወያይበት ጊዜም እንኳ ንግግራችን ማተኮር የሚገባው ‘ምሥራቹን’ በማወጁ ላይ ነው።—ሮሜ 10:15

5. በአገልግሎታችን ውጤታማ እንድንሆን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ሚና ይጫወታል?

5 በአምላክ ቃል ተጠቀሙ:- ኢየሱስ በሚያገለግልበት ጊዜ ሁሉ ቅዱሳን መጻሕፍትን ይጠቀም ነበር። ኢየሱስ ከራሱ ያስተማረው ምንም ነገር አልነበረም። (ዮሐ. 7:16, 18) የአምላክን ቃል ያነብ የነበረ ሲሆን የሰይጣንን ጥቃት ለመከላከልም ተጠቅሞበታል። (ማቴ. 4:1-4) ሌሎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተማር መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ልናነብና ያነበብነውን በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ልናደርግ ይገባል። (ሮሜ 2:21) በአገልግሎት ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ስንሰጥ የምንናገረው ነገር የቅዱሳን መጻሕፍት ድጋፍ እንዳለው ማብራራት የሚጠበቅብን ሲሆን አመቺ ሆኖ ሲገኝ በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማንበብ ይኖርብናል። የቤቱ ባለቤት እየነገርነው ያለነው የራሳችንን ሳይሆን የአምላክን ሐሳብ መሆኑን እንዲያስተውል ማድረግ ይኖርብናል።

6. ኢየሱስ የአድማጮቹን ልብ ለመንካት ምን አድርጓል?

6 በማስተማር ሥራችሁ የሰዎችን ልብ ለመንካት ጣሩ:- “እንደዚህ ሰው፣ ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም።” (ዮሐ. 7:46) ይህ፣ የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎች ኢየሱስን ለምን ይዘውት እንዳልመጡ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን በጠየቋቸው ጊዜ የሰጡት ምላሽ ነበር። ኢየሱስ እውቀትን ብቻ ከማስተላለፍ ይልቅ የሰዎችን ልብ በሚነካ መንገድ ያስተምር ነበር። (ሉቃስ 24:32) ኢየሱስ፣ ሰዎች መልእክቱን እንዲረዱ ለማድረግ ሲል ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ምሳሌ ይጠቀም ነበር። (ማቴ. 13:34) ኢየሱስ ከአቅማቸው በላይ የሆነ መረጃ በመስጠት አድማጮቹን አላስጨነቃቸውም። (ዮሐ. 16:12) የሰዎች ትኩረት በእሱ ላይ ሳይሆን በይሖዋ ላይ እንዲሆን ለማድረግ ይጥር ነበር። ልክ እንደ ኢየሱስ እኛም ጥሩ አስተማሪዎች መሆን የምንችለው ‘ለምናስተምረው ትምህርት ትኩረት’ የምንሰጥ ከሆነ ብቻ ነው።—1 ጢሞ. 4:16 NW

7. ኢየሱስ በአገልግሎቱ ወደፊት እንዲገፋ ያደረገው ምንድን ነው?

7 ሰዎች ግድ የለሽና ተቃዋሚ ቢሆኑም ወደፊት ግፉ:- ምንም እንኳ ኢየሱስ ተአምራትን ቢያደርግም ብዙዎች አልሰሙትም ነበር። (ሉቃስ 10:13) ሌላው ቀርቶ የገዛ ቤተሰቦቹ እንኳ ‘አእምሮውን እንደሳተ’ ተሰምቷቸው ነበር። (ማር. 3:21) ይሁን እንጂ ኢየሱስ በስብከቱ ሥራ ገፍቶበታል። ኢየሱስ፣ ሰዎችን ነፃ ማውጣት የሚችል እውነት እንደያዘ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ስለሆነ ለአገልግሎቱ አዎንታዊ አመለካከት ነበረው። (ዮሐ. 8:32) እኛም ይሖዋ እርዳታ እንደሚሰጠን ስለምንተማመን ተስፋ ላለመቁረጥ ቁርጥ ውሳኔ አድርገናል።—2 ቆሮ. 4:1

8, 9. ለምሥራቹ ስንል መሥዋዕትነት በመክፈል ረገድ የኢየሱስን ምሳሌ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው?

8 የተሟላ ተሳትፎ እንዲኖራችሁ አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ክፈሉ:- ኢየሱስ ለአገልግሎቱ ሲል ከቁሳዊ ነገሮች የሚገኝን ምቾት መሥዋዕት አድርጓል። (ማቴ. 8:20) ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል እስከ ምሽት የሰበከባቸው ጊዜያት ነበሩ። (ማር. 6:35, 36) ኢየሱስ ሥራውን ለመፈጸም ያለው ጊዜ ውስን እንደሆነ ያውቅ ነበር። “ዘመኑ አጭር” በመሆኑ እኛም የኢየሱስን ምሳሌ በመኮረጅ በግለሰብ ደረጃ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንን እና ሀብታችንን መሥዋዕት ማድረግ ያስፈልገናል።—1 ቆሮ. 7:29-31

9 በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ከኢየሱስ የተማሩ በመሆናቸው የተዋጣላቸው የምሥራቹ አገልጋዮች ነበሩ። (ሥራ 4:13) በታሪክ ዘመናት ሁሉ ከኖሩት የሚበልጠውን የታላቁን የወንጌል ሰባኪ የኢየሱስን ምሳሌ የምንኮርጅ ከሆነ አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ ለመፈጸም እንችላለን።—2 ጢሞ. 4:5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ