የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/08 ገጽ 3
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 8/08 ገጽ 3

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?፤ ጥቅምት:- መጽሔቶች እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? (ትራክት ቁጥር 26)፣ ኅዳር:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?

◼ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር በሚልኩት የጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ ላይ የ2009 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ፣ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2009 እና የ2009 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ ማዘዝ ይኖርባቸዋል።

◼ ቅርንጫፍ ቢሮው አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ጽሑፎችን ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት ጽሑፎች የትኞቹ እንደሆኑ እባካችሁ አትርሱ።

◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-23 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።

◼ ብሬይል ኖት ቴከር ወይም ጽሑፍ የሚያነብ ፕሮግራም ያላቸው ኮምፒውተሮችን የሚጠቀሙ ማየት የተሳናቸውንና የማየት ችግር ያለባቸውን አስፋፊዎች ወይም ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ለመርዳት ሲባል ከብሬይል የተገለበጠ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ኤሌክትሮኒክ ፋይል ማግኘት የሚቻልበት ዝግጅት አድርገናል። እነዚህ ፋይሎች ከሚያካትቷቸው ነገሮች መካከል በግሬድ 2 ወይም አጠር ተደርጎ በተጻፈ (contracted) ብሬይል የተዘጋጁ የሚበረከትና የጥናት የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ይገኙበታል። እነዚህ ፋይሎች የተዘጋጁት በእንግሊዝኛ ሲሆን ለሚያዝዙ ሁሉ በኢሜይል ይላክላቸዋል። የመጠበቂያ ግንብ መጽሔቶቹን ኤሌክትሮኒክ ፋይል ማግኘት የሚፈልጉ ካሉ የጉባኤው ጸሐፊ ለቅርንጫፍ ቢሮው ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው መጠየቅ ይኖርባቸዋል። በደብዳቤው ላይ የግለሰቡ ስምና አድራሻ፣ የሚጠቀምበት የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ስም ወይም ዓይነት፣ የኢሜይል አድራሻ እንዲሁም ብሬይል የሚያነበው በየትኛው ቋንቋ (እንግሊዝኛ፣ ስፓንኛ ወይም ፈረንሳይኛ) እንደሆነ መገለጽ ይኖርበታል። የኢሜይል አድራሻ ከሌለው ፋይሎቹን ተቀብሎ ሊያደርስለት የሚችል የሌላ ሰው የኢሜይል አድራሻ መላክ ይቻላል።

◼ በእጅ ያሉ ጽሑፎችና መጽሔቶች ዓመታዊ ቆጠራ በተቻለ መጠን ነሐሴ 31, 2008 ላይ ወይም ከዚያ ብዙም ሳይርቅ መደረግ ይኖርበታል። ይህ ቆጠራ የጽሑፍ አስተባባሪው በየወሩ ከሚያካሂደው ቆጠራ ጋር ተመሳሳይ ነው። የጽሑፎቹ ጠቅላላ ድምር የጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18) ላይ መሞላት አለበት። በእጅ ያሉ መጽሔቶችን ጠቅላላ ድምር ከመጽሔት አገልጋዩ(ዮቹ) ማግኘት ይቻላል። የአስተባባሪው ጉባኤ ጸሐፊ ቆጠራውን በበላይነት መከታተል ይኖርበታል። እሱና የአስተባባሪው ጉባኤ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች ቅጹ ላይ ይፈርማሉ። እያንዳንዱ አስተባባሪ ጉባኤ ሦስት የጽሑፍ ቆጠራ ቅጽ (S-18) ይደርሰዋል። እባካችሁ ዋናውን እስከ መስከረም 6 ድረስ ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ላኩ። ሁለተኛውን ደግሞ ፋይላችሁ ውስጥ አስቀምጡ። ሦስተኛውን ጊዜያዊ መሙያ አድርጋችሁ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ