ታኅሣሥ 14 የሚጀምር ሳምንት
ታኅሣሥ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 69 (160)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 6-8
ቁ. 1፦ ኢያሱ 8:1-17
ቁ. 2፦ ዓለም በውኃ ጠፋ—ዳግመኛ በውኃ ይጠፋ ይሆን? (lr ምዕ. 46)
ቁ. 3፦ በመክብብ 7:21, 22 ላይ የሚገኘው ምክር ጠቃሚ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 20 (45)
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ ስለ እምነቴ ለሌሎች መናገር የሚያስፈራኝ ለምንድን ነው? በሐምሌ 2009 ንቁ! ከገጽ 24-27 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ወላጆች በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማቸው ላይ ልጃቸው በትምህርት ቤት የሚያጋጥሙትን ጥያቄዎች እንዴት እንደሚመልስ ሲያዘጋጁት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በገጽ 25 ላይ ከሚገኙት ጥያቄዎች መካከል በአንዱ ላይ ምርምር ካደረጉ በኋላ ውይይት ያደርጉበታል። ከዚያም ልጁ ለጥያቄው እንዴት መልስ እንደሚሰጥ ለማየት ልምምድ ያደርጋሉ።
15 ደቂቃ፦ “በጥድፊያ ስሜት ስበኩ!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአንቀጽ 4 ላይ ስትወያዩ በቅንዓት ለሚያገለግል አንድ የመንግሥቱ አስፋፊ ቃለ ምልልስ አድርግ። የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቀው፦ አስፈላጊ ያልሆኑ የዓለም ጉዳዮች ሸክም እንዳይሆኑብህ ምን እርምጃዎችን ወስደሃል? በጥድፊያ ስሜት በመስበክህ ምን ጥቅሞች አግኝተሃል?
መዝሙር 42 (92)