የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የአውራጃ ስብሰባችን ባደረግንበት በጥቅምት ወር 8,607 አስፋፊዎችና አቅኚዎች ሪፖርት አድርገዋል። በአውራጃ ስብሰባ ላይ 15,984 የሚያህሉ ተሰብሳቢዎች ተገኝተው ነበር፤ ይህ ከፍተኛ ቁጥር እንዲገኝ ያስቻለው የአውራጃ ስብሰባ መጋበዣ ወረቀት በሰፊው በመሰራጨቱ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለመምራት ያደረግነው ጥረት ውጤት የሆኑ 270 ሰዎች መጠመቃቸው ደስታችንን ጨምሮልናል።