የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ የአገልግሎት ዓመት በመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ውስጥ በአስፋፊዎች ቁጥር ረገድ ከአንድ በመቶ በላይ ጭማሪ አግኝተናል። ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ልዑካን ለብሔራት አቀፍ ስብሰባ ወደ ኬንያ ሄደው የነበረ ቢሆንም በዚያ ወር በአገልግሎት ያሳለፍነው ሰዓት ቀደም ካሉት አራት ወራት ይበልጣል። ይሁንና ለተመላልሶ መጠየቅና መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንዳለብን የታወቀ ነው።
በታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ ለሦስተኛ ጊዜ በምናደርገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ ወንድሞችና እህቶች ከውጭ አገር መምጣት የጀመሩ ሲሆን በአገራችን የሚኖሩ በርካታ አስፋፊዎችና አቅኚዎች ከእነሱ ጋር ለማገልገል ማመልከቻ አስገብተዋል። በመጪዎቹ ወራት የምናደርገውን እንቅስቃሴ በታላቅ ጉጉት የምንጠባበቅ ከመሆኑም ሌላ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ሰዎች ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው አገልግሎት ይጀምራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።