የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በሚያዝያ ወር 8,811 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር የተመዘገበ ሲሆን እነዚህ አስፋፊዎች 6,600 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መርተዋል።
ከሚከተለው ተሞክሮ መመልከት እንደሚቻለው አሁንም እውነትን የተጠሙ በርካታ ሰዎች አሉ፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ርቆ በሚገኝ አንድ አዲስ ክልል የተመደቡ ሁለት ጊዜያዊ ልዩ አቅኚዎች በአሁኑ ሰዓት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻቸው ቁጥር 59 ደርሷል። በዚህ ቦታ በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ 70 ሰዎች ተገኝተው ነበር፤ በርካታ ሰዎች ለይሖዋ ምሥክሮች ያላቸው አክብሮት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የመንደሩ ነዋሪዎች በዕለት ተዕለት ንግግራቸው ላይ “ይሖዋ ይባርክህ!” የሚለውን ቃል አዘውትረው መጠቀም ጀምረዋል። በሦስቱ ወር መጨረሻ ላይ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ብቃቱን አሟልተው ያልተጠመቁ አስፋፊዎች ሆነዋል፤ ሌሎች ደግሞ መንፈሳዊ እድገት እያደረጉ ነው። ይህ ሁሉ የተከናወነው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ነው!
ደቀ መዛሙርት ለማድረጉ ሥራችን ይኸውም አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማግኘት ጸሎት የታከለበት ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥል!