የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ስድስት የወረዳና የልዩ ስብሰባዎች ቀርተውም እንኳ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ 503 የሚሆኑ ሰዎች ተጠምቀዋል። ምንም እንኳ በሰኔ ወር የአየሩ ጠባይ ዝናባማ ቢሆንም ከፍተኛ የአገልግሎት እንቅስቃሴ መደረጉ አስደስቶናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር የተሰጠው ሐሳብ ተግባራዊ መደረጉ ፍሬ አስገኝቷል፤ በሰኔ ወር 6,863 ጥናቶች የተመሩ ሲሆን ይህ ደግሞ በዓመቱ ውስጥ ሪፓርት ከተደረገው አኃዝ ከፍተኛው ነው። ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ነቅታችሁ በመከታተል ‘ማጠጣታችሁን’ ቀጥሉ።—1 ቆሮ. 3:6, 9