የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 25, 2011 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 7 እስከ ሚያዝያ 25, 2011 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ‘ከሌሎች አገር ዜጎች ብዙ ሕዝብ አይሁድ የሆኑት’ በምን መንገድ ነበር? (አስ. 8:17) [w06 3/1 ገጽ 11 አን. 3]
2. ሰይጣን በይሖዋ ፊት እንዲቆም የተፈቀደለት ለምንድን ነው? (ኢዮብ 1:6፤ 2:1) [w06 3/15 ገጽ 13 አን. 6፤ it-2-E ገጽ 16 አን. 4]
3. ሰይጣን “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን?” ብሎ ሲናገር ምን ማለቱ ነው? (ኢዮብ 1:9) [w94 11/15 ገጽ 11 አን. 6]
4. ይሖዋ “ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ” መሆኑን ማወቃችን በውስጣችን የመተማመን ስሜት እንዲኖረን የሚረዳን እንዴት ነው? (ኢዮብ 9:4) [w07 5/15 ገጽ 25 አን. 16፤ it-2-E ገጽ 1190 አን. 3]
5. ሰው ‘ክፋትን እንደ ውሃ ይጠጣል’ የሚለው የኤልፋዝ ንግግር የሰይጣንን አስተሳሰብ የሚያንጸባርቀው እንዴት ነው? (ኢዮብ 15:16) [w10 2/15 ገጽ 20 አን. 1-2]
6. በኢዮብ 19:2 ላይ ኢዮብ ከተናገራቸው የምሬት ቃላት ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? [w94 10/1 ገጽ 32 አን. 1-5]
7. ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን ጠብቆ እንዲኖር የረዳው ምንድን ነው? (ኢዮብ 27:5) [w09 4/15 ገጽ 6 አን. 17]
8. እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች በመርዳት ረገድ የኢዮብን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው? (ኢዮብ 29:12, 13) [w02 5/15 ገጽ 22 አን. 19፤ w94 9/15 ገጽ 24 አን. 1]
9. የኤሊሁ ምክር ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ከሰጡት ምክር የሚለየው እንዴት ነው? (ኢዮብ 33:1, 6) [w95 2/15 ገጽ 29 አን. 2]
10. በይሖዋ አስደናቂ ሥራዎች ላይ ማሰላሰላችን ምን ጥቅም አለው? (ኢዮብ 37:14) [w06 3/15 ገጽ 16 አን. 4]