የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በአገራችን ለአራተኛ ጊዜ የተደረገው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ በመጋቢት ወር የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህም ዘመቻ ጥሩ ውጤት ተገኝቷል። በዚህ ወር 9,095 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር አግኝተናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ረገድም 7,587 የደረሰ አዲስ ከፍተኛ ቁጥር በማግኘታችን ተደስተናል፤ ይህ አኃዝ ካለፈው ከፍተኛ የጥናቶች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር 6 በመቶ ጭማሪ አለው። ሁላችንም ሰዎች ጥናት እንዲጀምሩ እንድንጋብዝና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን እንድንመራ የቀረበልንን ሐሳብ ተግባራዊ ማድረጋችንን እንቀጥል!
ይህ መረጃ በተጠናቀረበት ጊዜ የሚያዝያ ወር ሪፖርት የደረሰን ባይሆንም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አስፋፊዎች በአቅኚነት አገልግሎት እየተካፈሉ በመሆኑ ይህ ወር በመንግሥቱ ሥራ ረገድ አስደናቂ ውጤት እንደሚገኝበት ሁኔታዎች ያመላክታሉ።