ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ መስከረም፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ጥቅምት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኙ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት አበርክቱለት፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ኅዳር፦ መጽሐፍ ቅዱስ—የያዘው መልእክት ምንድን ነው? ከዚህ ብሮሹር ጋር ወይም ደግሞ በዚህ ብሮሹር ፋንታ በሐምሌና በነሐሴ ወር ያበረከትነውን ማንኛውንም ባለ 32 ገጽ ብሮሹር መጠቀም ይቻላል። ታኅሣሥ፦ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው። የቤቱ ባለቤት ልጆች ካሉት ከታላቁ አስተማሪ ተማር ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባሉትን መጽሐፎች አበርክቱ።
◼ በ2012 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር ሚያዝያ 2 በሚጀምረው ሳምንት ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ ወደፊት ይገለጻል። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ሐሙስ ሚያዝያ 5, 2012 ከሚከበረው የመታሰቢያው በዓል በፊት መቅረብ አይኖርበትም።
◼ በመጋቢት 2012 ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ አስፋፊዎች በዚያ ወር እንደምርጫቸው 30 ወይም 50 ሰዓት ማገልገል ይችላሉ። በተጨማሪም የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን የሚጎበኘው በመጋቢት ወር ከሆነ በዚያ ወር ረዳት አቅኚ ሆነው የሚያገለግሉ አስፋፊዎች በሙሉ (ለማገልገል የመረጡት 30ም ሆነ 50 ሰዓት) የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ከዘወትር አቅኚዎች ጋር በሚያደርገው ስብሰባ ላይ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው መገኘት ይችላሉ።
◼ ከመስከረም ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚያቀርቡት የሕዝብ ንግግር “ደስተኛ ከሆኑት የአምላክ ሕዝቦች ጋር አንድነት መፍጠር” የሚል ርዕስ አለው።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ የ2010 የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! ጥራዞች፣ ትግርኛ፦ የሙታን መናፍስት።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ የአምላክ ወዳጅ፣ ኦሮምኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት።