ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ የካቲት፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ወይም መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? መጋቢት፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኙ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት አበርክቱለት፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ የመታሰቢያው በዓል ከተከበረ በኋላ ባለው እሁድ የሚሰጠው ልዩ ንግግር ርዕስ “መጨረሻው ሳታስቡት ይመጣባችሁ ይሆን?” የሚል ነው።
◼ ከየካቲት 1, 2012 እትም ጀምሮ የሚበረከተው የመጠበቂያ ግንብ እትም “መጽሐፍ ቅዱስን መማሪያዬ” የሚል ዓምድ ይዞ ይወጣል። ይህ ዓምድ፣ ዕድሜያቸው ሦስት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ያሏቸው ወላጆች እንዲጠቀሙበት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን “ልጆቻችሁን አስተምሩ” እና “ለታዳጊ ወጣቶች” ከተባሉት ዓምዶች ጋር እየተፈራረቀ ይወጣል።
◼ በዚህ የአገልግሎት ዓመት ዓለም አቀፍ ሪፖርት ላይ በስም ወዳልተጠቀሰ አገር ወይም በቅርብ በወጣው የዓመት መጽሐፍ የመጨረሻ ገጽ ላይ አድራሻው ወዳልተጠቀሰ አገር የመሄድ እቅድ በሚኖራችሁ ጊዜ ሁሉ ልታደርጉት የሚገባችሁን ጥንቃቄ ለማወቅ ወይም አስፈላጊውን መመሪያ ለማግኘት ቅርንጫፍ ቢሯችሁን እንድታነጋግሩ እናበረታታችኋለን። በዚያ አገር በመንግሥቱ ሥራ ላይ አንዳንድ እገዳዎች ተጥለው ሊሆን ይችላል። (ማቴ. 10:16) በአንዳንድ አገሮች ከሌላ አገር የመጡ እንግዶች በዚያ ከሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ወይም ጉባኤዎች ጋር ግንኙነት ማድረጋቸው ጥሩ ላይሆን ይችላል። ቅርንጫፍ ቢሮውን ስታማክሩ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስለ መመሥከር ወይም ጽሑፎችን ይዞ ስለመሄድ አንዳንድ መመሪያዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። የሚሰጣችሁን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ትብብር ማሳየታችሁ በራሳችሁ ላይም ሆነ በምትሄዱበት አገር ውስጥ በሚከናወነው የመንግሥቱ ሥራ ላይ አላስፈላጊ ችግር እንዳይፈጠር ያደርጋል።—1 ቆሮ. 14:33, 40