ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሚያዝያ እና ግንቦት፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኙ እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን ትራክት አበርክቱለት፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሰዎችን በምታነጋግሩበት በመጀመሪያው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ሐምሌ፦ ብሮሹሮች። ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባልን?፣ በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር!፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?፣ ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው—እንዴትስ ልታገኘው ትችላለህ?፣ የምትወዱት ሰው ሲሞት፣ የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?፣ ሪል ፌይዝ—ዩር ኪ ቱ ኤ ሃፒ ላይፍ (ለሙስሊሞች) እና ዘ ሮድ ቱ ኤቨርላስቲንግ ላይፍ—ሃቭ ዩ ፋውንድ ኢት?። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ።
◼ ጉባኤዎች የአውራጃ ስብሰባቸውን ለማድረግ አንድ ሳምንት ሲቀራቸው በሚያደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም ላይ ላይ ማስተካከያ በማድረግ የአውራጃ ስብሰባውን በሚመለከት በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በወጡት ምክሮችና ማሳሰቢያዎች ላይ መወያየት ይችላሉ። የአውራጃ ስብሰባውን ካደረጉ ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት የሚለውን ክፍል ተጠቅመው አስፋፊዎች ለአገልግሎት ጠቃሚ ሆነው ባገኟቸው ሐሳቦች ላይ ውይይት ማድረግ ይችላሉ።
◼ ወደ ሌላ አገር በምትሄዱበት ወቅት በዚያው በአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እቅድ ካላችሁ www.pr2711.com በተባለው ድረ ገጽ ላይ Lookup የሚለውን በመክፈት “Conventions” በሚለው ሥር ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ ዎችታወር ላይብረሪ 2011 በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ።