የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በሐምሌ ወር ከባድ ዝናብ የነበረ ቢሆንም በይሖዋ አገልግሎት ከሩብ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዓታት ማሳለፍ ችለናል፤ በተጨማሪም 9,408 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ተመዝግቧል። ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ባደረግናቸው የወረዳና የልዩ ስብሰባዎች 519 የሚያህሉ ሰዎች ተጠምቀዋል። ግሩም በሆነ መንገድ የተሠሩት የመንግሥት አዳራሾቻችን ሕይወት አድን ለሆነው የማስተማሩ ሥራችን ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል፤ ባለፉት አሥራ አንድ ወራት ዘጠኝ የመንግሥት አዳራሾች እንደተገነቡ ስንገልጽላችሁ ደስ ይለናል።