ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥር እና የካቲት፦ ከአምላክ የተላከ ምሥራች! ወይም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ። (አምላክን ስማ የሚለውን ብሮሹር፣ ማንበብ የማይችል ወይም የማንበብ ችሎታው ውስን የሆነ ሰውን ለማወያየት መጠቀም እንችላለን።) መጋቢት እና ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች።
◼ መጋዘናችን ውስጥ አዲስ የገቡ፦ መጽሐፍ ቅዱስ መማሪያዬ (ለትናንሽ ልጆች) በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሲዳምኛ፣ በትግርኛና በወላይትኛ፤ ትራክት ቁ. 30፣ 31፣ 32፣ 33፣ 34 እና 35 ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎች በርካታ ቋንቋዎች፤ በእምነታቸው ምሰሏቸው (አማርኛ፣ ቻይንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስዋሂሊ)፤ የምርምር መርጃ መሣሪያ (አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሲዳምኛ፣ ትግርኛ፣ ወላይትኛ)፤ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች—ጥራዝ 1 (አማርኛ)፤ ለውይይት የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች (ኦሮምኛ)፤ ተከታዬ ሁን (ኦሮምኛ)፤ አባካኙ ልጅ ተመለሰ!—በዲቪዲ (እንግሊዝኛ)፣ ምሥራቹን ለማወጅ የተደራጀ ሕዝብ/መላው የወንድማማች ማኅበር—በዲቪዲ (አማርኛ)
◼ የምርምር መርጃ መሣሪያ የተባለውን አዲስ ጽሑፍ በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ላይም ማግኘት እንደምትችሉ ስንገልጽላችሁ ደስ ይለናል። ጽሑፉ ኢንተርኔት ላይ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሲዳምኛ፣ በትግርኛ እና በወላይትኛ ይገኛል። ከእነዚህ ቋንቋዎች በአንዱ የተዘጋጀውን ቤተ መጻሕፍት ለማግኘት wol.jw.org ብላችሁ ህዝባር (/) በማድረግ የምትፈልጉትን ቋንቋ ምሕፃረ ቃል (AM፣ OM፣ SID፣ TI ወይም WAL) ጻፉ። ለምሳሌ ያህል፣ የአማርኛ ቤተ መጻሕፍት wol.jw.org/am በሚለው ሥር ይገኛል። በተጨማሪም ቤተ መጻሕፍቱን ማግኘት የሚቻልበት ሌላ ዘዴ አለ። jw.org/am በተባለው ድረ ገጽ ላይ “የሕትመት ውጤቶች” የሚለውን ክፈቱ፤ ከዚያም “የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት” የሚለውን ጠቅ አድርጉ። በዚህ መንገድ ቤተ መጻሕፍቱን ከከፈታችሁ በኋላ በስተ ቀኝ በኩል ከላይ ያለውን መምረጫ ተጠቅማችሁ የቤተ መጻሕፍቱን ቋንቋ መቀየር ትችላላችሁ።