የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በአውራጃ ስብሰባ ላይ ያገኘናቸው አዳዲስ ትራክቶች ተወዳጅነት አትርፈዋል። አሁን ትራክቶች ከብሮሹሮች ጋር አብረው ሪፖርት ስለሚደረጉ በኅዳር ወር በጠቅላላው 55,102 ብሮሹሮች ተበርክተዋል። ይህም በኅዳር 2012 ከተበረከቱ ብሮሹሮች በአራት እጥፍ ይበልጣል! ቅርንጫፍ ቢሯችን ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ ለማድረግ ዝግጅት ባደረገበት ወቅት ከአውሮፓና ከአሜሪካ የ55 ወንድሞችና እህቶች ማመልከቻ ስለደረሰን በጣም ተደስተናል።