ከሐምሌ 10-16
ሕዝቅኤል 15-17
መዝሙር 49 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“የገባኸውን ቃል ትጠብቃለህ?”፦ (10 ደቂቃ)
ሕዝ 17:1-4—ባቢሎናውያን በንጉሥ ዮአኪን ፋንታ ሴዴቅያስን አነገሡት (w07 7/1 12 አን. 6)
ሕዝ 17:7, 15—ሴዴቅያስ ለባቢሎን ታማኝ ለመሆን የገባውን መሐላ አፍርሶ ከግብፅ ወታደራዊ እርዳታ ጠየቀ (w07 7/1 12 አን. 6)
ሕዝ 17:18, 19—ይሖዋ፣ ሴዴቅያስ የገባውን ቃል እንዲያከብር ይጠብቅበት ነበር (w12 10/15 30 አን. 11፤ w88-E 9/15 17 አን. 8)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሕዝ 16:60—“ዘላቂ ቃል ኪዳን” የተባለው ምንድን ነው? በዚህ ቃል ኪዳን ውስጥ የተካተቱትስ እነማን ናቸው? (w88-E 9/15 17 አን. 7)
ሕዝ 17:22, 23—ይሖዋ እንደሚተክለው የተናገረው ‘ለጋ ቀንበጥ’ ማን ነው? (w07 7/1 12 አን. 6)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሕዝ 16:28-42
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) wp17.4 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) wp17.4 በሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ ለተበረከተለት ሰው—መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) fg ትምህርት 11 አን. 1-2—ግለሰቡ በስብሰባ ላይ እንዲገኝ ጋብዝ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
በትዳራችሁ ደስታ ብታጡ እንኳ የጋብቻ ቃል ኪዳናችሁን ፈጽሙ፦ (10 ደቂቃ) በመጋቢት 2014 ንቁ! ከገጽ 14-15 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
የይሖዋ ወዳጅ ሁን—እውነቱን ተናገር፦ (5 ደቂቃ) የይሖዋ ወዳጅ ሁን—እውነቱን ተናገር የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም አስቀድመህ የመረጥካቸውን ጥቂት ልጆች ወደ መድረኩ እንዲወጡ ካደረክ በኋላ ስለ ቪዲዮው ጠይቃቸው።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr ምዕ. 12 አን. 9-15፤ “ከበላይ ተመልካችነት ጋር በተያያዘ የተደረጉ መሻሻሎች” እና “የበላይ አካሉ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያከናውነው እንዴት ነው?” የሚሉት ሣጥኖች
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 73 እና ጸሎት