ከሐምሌ 24-30
ሕዝቅኤል 21-23
መዝሙር 14 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ንግሥና የሚገባው ሕጋዊ መብት ያለው ነው”፦ (10 ደቂቃ)
ሕዝ 21:25—“መጥፎው የእስራኤል አለቃ” ንጉሥ ሴዴቅያስ ነው (w07 7/1 13 አን. 11)
ሕዝ 21:26—በኢየሩሳሌም ሆነው የሚገዙ የዳዊት ዘር ነገሥታት የንግሥና መስመር ይቋረጣል (w11 8/15 9 አን. 6)
ሕዝ 21:27—“ሕጋዊ መብት ያለው” ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (w14 10/15 10 አን. 14)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሕዝ 21:3— ይሖዋ ከሰገባው የሚመዝዘው ‘ሰይፍ’ ምንድን ነው? (w07 7/1 14 አን. 1)
ሕዝ 23:49—በምዕራፍ 23 ላይ ጎላ ተደርጎ የተገለጸው እስራኤላውያን የሠሩት ስህተት ምንድን ነው? እኛስ ምን ትምህርት እናገኛለን? (w07 7/1 14 አን. 6)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሕዝ 21:1-13
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) fg—መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።)
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bh—ለመጽሔት ደንበኛህ መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።)
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bh 215 አን. 3–216 አን. 1
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት”፦ (15 ደቂቃ) የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ በውይይት የሚያቀርበው። ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚያሳየውን ቪዲዮውን በማጫወት ክፍሉን ጀምር።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr “ክፍል 4—መንግሥቱ የተቀዳጃቸው ድሎች—ምሥራቹ በሕግ የጸና እንዲሆን ማድረግ” እና ምዕ. 13 አን. 1-10
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 34 እና ጸሎት