የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 ሰኔ ገጽ 8
  • ከግል ጥናትህ የበለጠ ጥቅም ማግኘት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከግል ጥናትህ የበለጠ ጥቅም ማግኘት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥናት በረከት ያስገኛል
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • ጥናት—አስደሳችና የሚክስ ሥራ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • የነገሥታትን ምሳሌ ተከተል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ማዳበር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 ሰኔ ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ከግል ጥናትህ የበለጠ ጥቅም ማግኘት

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? በአምላክ ቃል ላይ የምናደርገው የግል ጥናት የእውነት “ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ” በሚገባ ለመረዳት ያስችለናል። (ኤፌ 3:18) በተጨማሪም በዚህ ክፉ ዓለም ውስጥ እንከንና እድፍ የሌለብን ሆነን እንድንኖር እንዲሁም ‘የሕይወትን ቃል አጥብቀን መያዝ’ እንድንችል ይረዳናል። (ፊልጵ 2:15, 16) የግል ጥናት፣ በግለሰብ ደረጃ የሚያስፈልገንን ትምህርት መርጠን ለማጥናት አጋጣሚ ይሰጠናል። የአምላክን ቃል በማንበብና በማጥናት ከምናሳልፈው ጊዜ፣ የበለጠ ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ እንችላለን?

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ለማጥናት በምትጠቀምበት መጽሐፍ ቅዱስ (በታተመውም ሆነ በኤሌክትሮኒክ ፎርማት በተዘጋጀው) ጥቅሶች ላይ ማስመር እንዲሁም ማስታወሻ ማስፈር ጠቃሚ ነው

  • የአምላክን ቃል ስታነብ ‘ማን? ምን? መቼ? የት? ለምን? እንዴት?’ እያልክ ራስህን ጠይቅ

  • የተሟላ መረጃ ለማግኘት ሞክር። በተዘጋጁልን የምርምር መሣሪያዎች ተጠቅመህ በርዕሰ ጉዳይ ወይም በጥቅስ ምርምር አድርግ

  • ትምህርቱን በግልህ እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምትችል ለማስተዋል፣ ባነበብከው ነገር ላይ አሰላስል

  • የተማርከውን ነገር በሕይወትህ ተግባራዊ አድርግ።—ሉቃስ 6:47, 48

ውጤታማ የሆነ የግል ጥናት በማድረግ እውነትን ‘አጥብቆ መያዝ’ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አንዳንዶች የግል ጥናትን በተመለከተ ምን ብለዋል?

  • የግል ጥናት ማድረግ ከመጀመራችን በፊት ምንጊዜም መጸለያችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ በደንብ መረዳት እንድንችል ምን ሊያግዘን ይችላል?

  • ለጥናት በምንጠቀምበት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምን ዓይነት ምልክቶች ማድረግ እንችላለን?

  • የአምላክን ቃል ስናጠና ማሰላሰላችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • የተማርነውን ነገር ምን ልናደርግ ይገባል?

አንዲት እህት ጥልቀት ያለው የግል ጥናት ስታደርግ፤ አንድ ወንድም የተለያዩ ቀለማት በመጠቀም በመጽሐፍ ቅዱሱ ላይ ምልክት ሲያደርግ፤ አንዲት እህት በመጽሐፍ ቅዱሷ ላይ ያሰፈረችውን ማስታወሻ ለሁለት ሰዎች ስታሳይ፤ አንድ ወንድም ሲጸልይ

“ሕግህን ምንኛ ወደድኩ! ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ።”—መዝ 119:97

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ