ከሐምሌ 1-7
ቆላስይስ 1-4
መዝሙር 56 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“አሮጌውን ስብዕና ገፋችሁ ጣሉ እንዲሁም አዲሱን ስብዕና ልበሱ”፦ (10 ደቂቃ)
[የቆላስይስ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ቆላ 3:5-9—“አሮጌውን ስብዕና . . . ገፋችሁ ጣሉ” (w11 3/15 10 አን. 12-13)
ቆላ 3:10-14—“አዲሱን ስብዕና ልበሱ” (w13 9/15 21 አን. 18-19)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ቆላ 1:13, 14—‘የሚወደው ልጁ መንግሥት’ ምንድን ነው? (it-2 169 አን. 3-5)
ቆላ 2:8—‘የዓለም መሠረታዊ ነገሮች’ ምንድን ናቸው? (w08 8/15 28 አን. 9)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ትክክለኛ እና አሳማኝ መረጃ የሚለውን ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ማስተማር ከተባለው ብሮሹር ላይ ጥናት 7ን ተወያዩበት።
ንግግር፦ (5 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) w04 5/1 19-20 አን. 3-7—ጭብጥ፦ አንዳንድ ክርስቲያኖች ለጳውሎስ “የብርታት ምንጭ” የሆኑለት እንዴት ነው? (ቆላ 4:11) (th ጥናት 7)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
የ2018 የትምህርት ኮሚቴ ሪፖርት፦ (15 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ ድርጅታችን በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ጉዞ ምን ቦታ አለው? በዋናው መሥሪያ ቤት የሚገኘው የጉዞ ዲፓርትመንት በመዋጮ የሚገኘውን ገንዘብ ለመቆጠብ ጥረት የሚያደርገው እንዴት ነው? አስፋፊዎች፣ ድርጅቱ ከጉዞ ጋር በተያያዘ የሚያወጣውን ወጪ ለመቀነስ ምን ማድረግ ይችላሉ? በዋናው መሥሪያ ቤት የሚገኘው የጉዞ ዲፓርትመንት፣ በ2019 በሚደረጉት ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ወደተለያዩ ቦታዎች የሚጓዙ ልዑካንን ለመርዳት ምን እያደረገ ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 64
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 130 እና ጸሎት