የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 ነሐሴ ገጽ 8
  • የምታከናውኑት መልካም ሥራ አይረሳም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምታከናውኑት መልካም ሥራ አይረሳም
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከሁሉ የተሻለ የሥራ መስክ ይሆንልህ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ራስህን በፈቃደኝነት ልታቀርብ ትችላለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • “የአምላክን ቤት” በአድናቆት መመልከት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ይምጡና ይጎብኙ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 ነሐሴ ገጽ 8
በቤቴል የምታገለግል አንዲት እህት ኩሽና ውስጥ እየሠራች

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የምታከናውኑት መልካም ሥራ አይረሳም

የይሖዋ ሕዝቦች በሙሉ ለአምላካችን ቅዱስ አገልግሎት በማቅረብ የማይረሳ ታሪክ ማስመዝገብ ይችላሉ። አንድ አፍቃሪ ወላጅ ልጆቹ ያከናወኑትን መልካም ሥራ ምንጊዜም ከፍ አድርጎ እንደሚመለከት ሁሉ ይሖዋም የምናከናውነውን ሥራ እንዲሁም ለስሙ የምናሳየውን ፍቅር መቼም ቢሆን አይረሳም። (ማቴ 6:20፤ ዕብ 6:10) እርግጥ ነው፣ የእያንዳንዳችን ችሎታና ሁኔታ ይለያያል። ያም ቢሆን በይሖዋ አገልግሎት ምርጣችንን የምንሰጥ ከሆነ ደስታ እናገኛለን። (ገላ 6:4፤ ቆላ 3:23) ባለፉት ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞችና እህቶች በቤቴል አገልግለዋል። በቤቴል ለማገልገል ራስህን በፈቃደኝነት ማቅረብ ትችላለህ? ካልሆነ በዚህ አገልግሎት እንዲካፈል ልታበረታታው የምትችለው ሰው አለ? ወይም የቤቴል ቤተሰብ አባል የሆነ ክርስቲያን በዚህ አገልግሎቱ እንዲቀጥል መርዳት ትችል ይሆን?

ለቤቴል አገልግሎት ራስህን ማቅረብ ትችል ይሆን? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አንድ ክርስቲያን በቤቴል ለማገልገል ራሱን እንዲያቀርብ ሊያነሳሳው የሚገባው ምንድን ነው?

  • በቤቴል ማገልገል ስለሚያስገኛቸው በረከቶች አንዳንዶች ምን ብለዋል?

  • በቤቴል ለማገልገል የሚያስፈልጉት ብቃቶች ምንድን ናቸው?

  • በቤቴል ለማገልገል ማመልከት የምትችለው እንዴት ነው?

ኮምፒውተር ላይ በቡድን ሆነው የሚሠሩ ሦስት ቤቴላውያን፣ ጽሑፎችን በካርቶን የሚያሽግ ወንድም፣ ቤቴል ውስጥ የእንጨት ሥራ የሚሠራ ወንድም

በቤቴል ለማገልገል የሚያስፈልጉ ብቃቶች

  • ለይሖዋና ለድርጅቱ ጥልቅ ፍቅር ያለው

  • የላቀ የሥነ ምግባር አቋምና በይሖዋ ፊት ንጹሕ ሕሊና ያለው

  • ለክርስቲያን አገልጋዮች የሚመጥን አለባበስና አጋጌጥ ያለው

  • ለክርስቲያኖች ተገቢ የሆነ መዝናኛ የሚመርጥ

  • በአብዛኛው ከ19 እስከ 35 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ

  • አእምሯዊ፣ ስሜታዊና አካላዊ ጤንነቱ ጥሩ የሆነ

  • በቅርንጫፍ ቢሮው ውስጥ በሚሠራበት ቋንቋ ማንበብና መጻፍ እንዲሁም ቋንቋውን መናገር የሚችል

  • ቢያንስ ለአንድ ዓመት በቤቴል ለመቆየት ፈቃደኛ የሆነ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ