ክርስቲያናዊ ሕይወት
ምድሪቱ ‘ወንዙን ዋጠች’
ባለፉት የታሪክ ዘመናት እንደታየው፣ ሰብዓዊ ባለሥልጣናት በተለያዩ አጋጣሚዎች የይሖዋን ሕዝቦች ረድተዋል። (ዕዝራ 6:1-12፤ አስ 8:10-13) በዘመናችንም ቢሆን “ምድሪቱ” (በዚህ ሥርዓት ውስጥ ያሉ ምክንያታዊ አመለካከት ያላቸው ባለሥልጣናት) “ዘንዶው” ማለትም ሰይጣን ዲያብሎስ ያስነሳውን የስደት ወንዝ ስትውጥ ተመልክተናል። (ራእይ 12:16) “አዳኝ አምላካችን” የሆነው ይሖዋ ሕዝቡን እንዲረዱ ሰብዓዊ ገዢዎችን የሚያነሳሳበት ጊዜ አለ።—መዝ 68:20፤ ምሳሌ 21:1
ይሁንና በእምነትህ ምክንያት ለእስር ብትዳረግስ? የይሖዋ ጥበቃ እንደማይለይህ ፈጽሞ አትጠራጠር። (ዘፍ 39:21-23፤ መዝ 105:17-20) ላሳየኸው እምነት ወሮታ እንደምታገኝና ንጹሕ አቋምህን መጠበቅህ በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞችህን እንደሚያበረታታ እርግጠኛ ሁን።—ፊልጵ 1:12-14፤ ራእይ 2:10
የኮሪያ ወንድሞች ከእስር ተፈቱ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ባለፉት ዓመታት በደቡብ ኮሪያ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን የታሰሩት ለምን ነበር?
አንዳንዶቹ ወንድሞቻችን የተፈረደባቸውን የእስር ጊዜ ሳይጨርሱ እንዲፈቱ ያስቻለው የትኛው የፍርድ ቤት ውሳኔ ነው?
በአሁኑ ጊዜ በእምነታቸው ምክንያት እስር ቤት ያሉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወንድሞቻችንን መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?
አሁን ያለንን ነፃነት እንዴት ልንጠቀምበት ይገባል?
በፍርድ ቤት ከምናገኘው ከየትኛውም ድል በስተጀርባ ያለው ማን ነው?
ነፃነቴን እየተጠቀምኩበት ያለሁት እንዴት ነው?