ከሐምሌ 20-26
ዘፀአት 10–11
መዝሙር 65 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ሙሴና አሮን ታላቅ ድፍረት አሳይተዋል”፦ (10 ደቂቃ)
ዘፀ 10:3-6—ሙሴና አሮን ስምንተኛው መቅሰፍት እንደሚመጣ በድፍረት ለፈርዖን ተናገሩ (w09 7/15 20 አን. 6)
ዘፀ 10:24-26—ፈርዖን ከአምላክ ትእዛዛት መካከል ከፊሉን ብቻ እንዲታዘዙ ጫና ቢያደርግባቸውም ሙሴና አሮን ፈቃደኛ አልሆኑም
ዘፀ 10:28፤ 11:4-8—ሙሴና አሮን አሥረኛው መቅሰፍት እንደሚመጣ ያለፍርሃት ተናገሩ (it-2 436 አን. 4)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (10 ደቂቃ)
ዘፀ 10:1, 2—ወላጆች ከዚህ ጥቅስ ምን ትምህርት ያገኛሉ? (w95 9/1 11 አን. 11)
ዘፀ 11:7—ይሖዋ “በእስራኤላውያን ላይ . . . ውሻ እንኳ አይጮኽም” ሲል ምን ማለቱ ነበር? (it-1 783 አን. 5)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋ አምላክን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ዘፀ 10:1-15 (th ጥናት 10)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ አስፋፊው የቤቱን ባለቤት ካስረዳበት መንገድ ምን ትምህርት አግኝታችኋል? አስፋፊው በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ አንድ ጽሑፍ ሊያስተዋውቅ ይችል የነበረው እንዴት ነው?
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ግለሰቡ በስብሰባ ላይ እንዲገኝ ጋብዝ። (th ጥናት 8)
ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ አንድ ጽሑፍ አበርክት። (th ጥናት 12)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ፍጥረት ስለ ድፍረት ምን ያስተምረናል?”፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ከፍጥረት ድፍረትን ተማሩ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) jy ምዕ. 115
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
መዝሙር 124 እና ጸሎት