የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 ጥር ገጽ 8-9
  • ከጥር 29–የካቲት 4

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥር 29–የካቲት 4
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 ጥር ገጽ 8-9

ከጥር 29–የካቲት 4

ኢዮብ 40–42

መዝሙር 124 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ከኢዮብ ታሪክ የምናገኛቸው ትምህርቶች

(10 ደቂቃ)

የእናንተ እይታ ከይሖዋ እይታ ጋር ሲነጻጸር የተገደበ እንደሆነ አምናችሁ ተቀበሉ (ኢዮብ 42:1-3፤ w10 10/15 3-4 አን. 4-6)

ይሖዋና ድርጅቱ የሚሰጧችሁን ምክር በፈቃደኝነት ተቀበሉ (ኢዮብ 42:5, 6፤ w17.06 25 አን. 12)

ይሖዋ ፈተና ቢያጋጥማቸውም ለእሱ ያላቸውን ታማኝነት የሚጠብቁ ሰዎችን ይባርካል (ኢዮብ 42:10-12፤ ያዕ 5:11፤ w22.06 25 አን. 17-18)

ኢዮብና ሚስቱ በአድናቆት እርስ በርስ ሲተያዩ። ኢዮብ ወደ ከብቶቻቸውና ወደ ቤታቸው እየጠቆመ ነው።

ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን በመጠበቁ ይሖዋ ባርኮታል

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢዮብ 42:7—የኢዮብ ሦስት ጓደኞች መጥፎ ነገር የተናገሩት በማን ላይ ነው ሊባል ይችላል? ይህን ማወቃችን የሚደርስብንን ፌዝ ለመቋቋም የሚረዳንስ እንዴት ነው? (it-2 808)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) ኢዮብ 42:1-17 (th ጥናት 11)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ የክርስትና እምነት ተከታይ አይደለም። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 3)

5. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 13 ነጥብ 6-7 እና አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ (lmd ምዕራፍ 11 ነጥብ 4)

6. ንግግር

(4 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 2—ጭብጥ፦ ምድር ፈጽሞ አትጠፋም። (th ጥናት 13)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 108

7. ሌሎች የይሖዋን ፍቅር እንዲያጣጥሙ እርዷቸው

(15 ደቂቃ) ውይይት።

“በይሖዋ ቤተሰብ ውስጥ ክርስቲያናዊ ፍቅር አግኝተናል” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ሚሚ እና እናቷ ሆስፒታል ለተኛች እህት አበባ እና ፖስት ካርድ ሲወስዱ።

ፍቅር የሆነ አምላክ ማምለክ በመቻላችን በጣም ደስተኞች ነን። (1ዮሐ 4:8, 16) ይሖዋ አፍቃሪ አምላክ መሆኑ ወደ እሱ እንድንቀርብ እንዲሁም የእሱ ወዳጆች ሆነን እንድንኖር ያነሳሳናል። የይሖዋ በጎች እንደመሆናችን መጠን ሁላችንም ይሖዋ እንደሚወደን ይሰማናል።

ከቤተሰባችን አባላት፣ ከእምነት አጋሮቻችን እንዲሁም ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት የይሖዋን ፍቅር ለማንጸባረቅ አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እናደርጋለን። (ኢዮብ 6:14፤ 1ዮሐ 4:11) ፍቅር ማሳየታችን ሌሎች ይሖዋን እንዲያውቁና ወደ እሱ እንዲቀርቡ ሊያነሳሳቸው ይችላል። በአንጻሩ ደግሞ ለሌሎች ፍቅር የማናሳይ ከሆነ የይሖዋን ፍቅር ማጣጣም ሊከብዳቸው ይችላል።

በይሖዋ ቤተሰብ ውስጥ ክርስቲያናዊ ፍቅር አግኝተናል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

ፍቅር ማሳየት ያለውን አስፈላጊነት በተመለከተ ከሌይ ሌይ እና ከሚሚ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

የእምነት አጋሮቻችን የይሖዋን ፍቅር እንዲያጣጥሙ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

  • የይሖዋ ውድ በጎች እንደሆኑ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው።—መዝ 100:3

  • በሚያንጽ መንገድ አነጋግሯቸው።—ኤፌ 4:29

  • ስሜታቸውን ለመረዳት ጥረት አድርጉ።—ማቴ 7:11, 12

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 5 አን. 1-8፣ በገጽ 39 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 126 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ