የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb24 መጋቢት ገጽ 2-3
  • ከመጋቢት 4-10

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከመጋቢት 4-10
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2024
mwb24 መጋቢት ገጽ 2-3

ከመጋቢት 4-10

መዝሙር 16–17

መዝሙር 111 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “ይሖዋ . . . ለእኔ የጥሩ ነገሮች ምንጭ አንተ ነህ”

(10 ደቂቃ)

ይሖዋን ከሚያገለግሉ ሰዎች ጋር የመሠረትነው ወዳጅነት ደስታ ያስገኝልናል (መዝ 16:2, 3፤ w18.12 26 አን. 11)

ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ያለን መሆኑ እርካታ ያስገኝልናል (መዝ 16:5, 6፤ w14 2/15 29 አን. 4)

ይሖዋ የሚያደርግልን መንፈሳዊ ጥበቃ ያለስጋት እንድንኖር ያደርገናል (መዝ 16:8, 9፤ w08 2/15 3 አን. 2-3)

ሁለት እህቶች በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሲተቃቀፉ። ሌሎችም ፈገግ ብለው ወደ እነሱ እየመጡ ነው።

ሕይወታችን የጥሩ ነገሮች ምንጭ በሆነው በይሖዋ አምልኮ ዙሪያ ያጠነጠነ ስለሆነ እንደ ዳዊት ትርጉም ያለው ሕይወት እንመራለን።

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ወደ እውነት ከመጣሁ በኋላ ሕይወቴ የተሻሻለው እንዴት ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 17:8—“እንደ ዓይንህ ብሌን” የሚለው አገላለጽ ምን ትርጉም አለው? (w24.01 27 አን. 6)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 17:1-15 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(1 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ አበርክት። (th ጥናት 11)

5. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ አበርክት። ግለሰቡ ፍላጎት ካሳየ በኋላ የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (th ጥናት 9)

6. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የመታሰቢያውን በዓል መጋበዣ አበርክት። (th ጥናት 2)

7. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 14 ማስተዋወቂያ እና ነጥብ 1-3 (th ጥናት 6)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 20

8. ለመታሰቢያው በዓል መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ጠረጴዛ ላይ ቂጣና ቀይ የወይን ጠጅ ተቀምጦ።

ኢየሱስ የሰጠንን ትእዛዝ በመከተል እሁድ፣ መጋቢት 24 የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ እናከብራለን። የኢየሱስ ሞት ይሖዋና ኢየሱስ ታላቅ ፍቅር ያሳዩበት ዝግጅት ነው። (ሉቃስ 22:19፤ ዮሐ 3:16፤ 15:13) ለዚህ ልዩ በዓል ራሳችንን ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

  • ሰዎችን ለልዩ ንግግሩና ለመታሰቢያው በዓል ለመጋበዝ በምናደርገው ዘመቻ ላይ በቅንዓት ተካፈል። ልትጋብዛቸው የምትችላቸውን ሰዎች በዝርዝር ጻፍና ጋብዛቸው። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ የሚኖሩት ከጉባኤህ ክልል ውጭ ከሆነ እነሱ በሚኖሩበት አካባቢ የመታሰቢያው በዓል የሚከበርበትን ሰዓትና ቦታ ለማወቅ jw.org​ን ተመልከት

  • በመጋቢትና በሚያዝያ ወራት የአገልግሎት እንቅስቃሴህን አሳድግ። ለ15 ወይም ለ30 ሰዓት በማገልገል ረዳት አቅኚ መሆን ትችላለህ?

  • ከመጋቢት 18 ጀምሮ ኢየሱስ በምድር ላይ ባሳለፈው የመጨረሻ ሳምንት የተከናወኑትን ወሳኝ ክንውኖች አንብብ። በገጽ 6-7 ላይ ከሚገኘው “የ2024 የመታሰቢያው በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም” ላይ በየቀኑ ምን ያህል እንደምታነብ መወሰን ትችላለህ

  • በመታሰቢያው በዓል ቀን jw.org ላይ የሚወጣውን ልዩ የማለዳ አምልኮ ፕሮግራም ተመልከት

  • በመታሰቢያው በዓል ላይ የሚገኙ አዲሶችንና የቀዘቀዙ ክርስቲያኖችን ሞቅ አድርገህ ተቀበል። ከበዓሉ በኋላ፣ ጥያቄ ካላቸው መልስላቸው። ከእነሱ ጋር ቀጣይ ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ያዝ

  • ከመታሰቢያው በዓል በፊትና በኋላ በቤዛው ላይ አሰላስል

የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

በመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ ላይ ይህን ቪዲዮ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

9. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 6 አን. 18-24፣ በገጽ 48 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 73 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ