የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb25 ጥር ገጽ 6-7
  • ከጥር 27–የካቲት 2

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከጥር 27–የካቲት 2
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2025
mwb25 ጥር ገጽ 6-7

ከጥር 27–የካቲት 2

መዝሙር 140–143

መዝሙር 44 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. እርዳታ ለማግኘት ካቀረባችሁት ልመና ጋር የሚስማማ እርምጃ ውሰዱ

(10 ደቂቃ)

ምክርና እርማት ለመቀበል ፈቃደኞች ሁኑ (መዝ 141:5፤ w22.02 12 አን. 13-14)

በይሖዋ የማዳን ሥራዎች ላይ አሰላስሉ (መዝ 143:5፤ w10 3/15 32 አን. 4)

የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ለማዳበር ጥረት አድርጉ (መዝ 143:10፤ w15 3/15 32 አን. 2)

አንድ ወጣት ወንድም የግል ጥናት ሲያደርግ። ሥዕሎች፦ 1. ደጅ ሆኖ ሲጸልይ። 2. ከአንድ አረጋዊ ወንድም ጋር አብሮ እያገለገለ የተሰጠውን ምክር ሲያዳምጥ።

ከመዝሙር 140–143 ዳዊት እርዳታ ለማግኘት ያቀረበውን ልመና ብቻ ሳይሆን ከልመናው ጋር የሚስማማ እርምጃ እንደወሰደ የሚያሳዩ ሐሳቦችንም ይዟል።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 140:3—ዳዊት የክፉ ሰዎችን ምላስ ከእባብ ምላስ ጋር ያመሳሰለው ለምንድን ነው? (it-2 1151)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

(4 ደቂቃ) መዝ 141:1-10 (th ጥናት 12)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ለግለሰቡ ተግባራዊ እርዳታ ከሰጠህ በኋላ ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ግለሰቡ ሥራ እንደሚበዛበት ይነግርሃል። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 3)

6. እምነታችንን ማብራራት

(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwfq ርዕስ 21—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ደም የማይወስዱት ለምንድን ነው? (th ጥናት 7)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 141

7. የሕክምና እርዳታ ወይም ቀዶ ጥገና ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ተዘጋጁ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ “በጭንቅ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስልን ረዳታችን” እንደሚሆን ቃል ገብቶልናል። (መዝ 46:1) የሕክምና እርዳታ ወይም ቀዶ ጥገና የሚጠይቁ ሁኔታዎች ጭንቀት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ይሁንና ይሖዋ እንዲህ ላሉ ሁኔታዎች ለመዘጋጀት የሚያስፈልገንን ነገር በሙሉ አዘጋጅቶልናል። ለምሳሌ ድርጅቱ የሕክምና መመሪያ ካርድ (DPA)፣ የመታወቂያ ካርድa እና የሕክምና መረጃ የሚሰጡ ሌሎች ሰነዶችንb እንዲሁም የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴዎችን አዘጋጅቶልናል። እነዚህ ዝግጅቶች ይሖዋ ከደም ጋር በተያያዘ ያወጣውን ሕግ እንድናከብር ይረዱናል።—ሥራ 15:28, 29

አንዲት እህት የሕክምና መመሪያ ካርድ ስትሞላ።

የሕክምና እርዳታ ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ተዘጋጅታችኋል? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • አንዳንዶች የሕክምና መመሪያ ካርድ መሙላታቸው የጠቀማቸው እንዴት ነው?

  • ለነፍሰ ጡር እናቶች የተሰጠ መረጃ (S-401) የሚለው ሰነድ አንዳንዶችን የረዳቸው እንዴት ነው?

  • ሆስፒታል መተኛት፣ ቀዶ ሕክምና ማድረግ ወይም እንደ ካንሰር ሕክምና ያለ ሌላ ሕክምና ማግኘት የሚያስፈልገን ከሆነ ሕክምናው ከደም ጋር የተያያዘ ጥያቄ እንደሚያስነሳ ባይሰማንም እንኳ በተቻለ ፍጥነት የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴውን ማነጋገራችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ተዘጋጅታችኋል?

  • ውሳኔያችሁን በሕክምና መመሪያ ካርዳችሁ ላይ አስፍሩ

  • በተቻለ ፍጥነት የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴውን አነጋግሩ

  • ደም ከመውሰድ፣ የደም ንዑሳን ክፍልፋዮችን ከመጠቀም እንዲሁም የራሳችሁን ደም መጠቀም ከሚጠይቁ ሕክምናዎች ጋር በተያያዘ ያላችሁን አቋም ለሐኪማችሁ ለማስረዳት ዝግጁ ሁኑ።—lff ምዕራፍ 39⁠ን ተመልከት

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 21 አን. 14-22

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 103 እና ጸሎት

a የተጠመቁ አስፋፊዎች የሕክምና መመሪያ ካርዱን ከጽሑፍ አገልጋዩ ማግኘት ይችላሉ፤ በተጨማሪም ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆቻቸው የመታወቂያ ካርድ መውሰድ ይችላሉ።

b ለነፍሰ ጡር እናቶች የተሰጠ መረጃ (S-401)፣ ቀዶ ሕክምና ወይም ኬሞቴራፒ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የተሰጠ መረጃ (S-407) እንዲሁም የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ልጅ ላላቸው ወላጆች የተዘጋጀ መረጃ (S-55) የተባሉት ሰነዶች ሲያስፈልጓችሁ ሽማግሌዎቻችሁን መጠየቅ ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ