የጥናት ፕሮጀክት
በይሖዋ የማዳን ኃይል ላይ ያለህን እምነት አጠናክር
ዘኁልቁ 13:25–14:4ን አንብብ፤ ከዚያም እስራኤላውያን በይሖዋ ሳይታመኑ የቀሩት እንዴት እንደሆነ ልብ በል።
አውዱን መርምር። ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያን ይሖዋ እነሱን የማዳን ችሎታ እንዳለው መተማመን የነበረባቸው ለምንድን ነው? (መዝ. 78:12-16, 43-53) በይሖዋ ላይ የነበራቸውን እምነት እንዲያጡ ያደረጋቸው ምንድን ነው? (ዘዳ. 1:26-28) ኢያሱና ካሌብ በይሖዋ እንደሚታመኑ ያሳዩት እንዴት ነው?—ዘኁ. 14:6-9
በጥልቀት ምርምር አድርግ። እስራኤላውያን በይሖዋ ላይ ያላቸውን እምነት ለማሳደግ ምን ማድረግ ይችሉ ነበር? (መዝ. 9:10፤ 22:4፤ 78:11) በይሖዋ በመታመንና እሱን በማክበር መካከል ምን ግንኙነት አለ?—ዘኁ. 14:11
ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦
‘ሙሉ በሙሉ በይሖዋ መታመን የሚከብደኝ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነው?’
‘አሁንም ሆነ ወደፊት በይሖዋ ይበልጥ መታመን የምችለው እንዴት ነው?’
‘ታላቁ መከራ ሲቃረብ ስለ ምን ነገር እርግጠኛ መሆን እችላለሁ?’—ሉቃስ 21:25-28