የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwwd ርዕስ 3
  • አስደናቂው የኦክቶፐስ እጅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስደናቂው የኦክቶፐስ እጅ
  • ንድፍ አውጪ አለው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዳኝ በሆነው የይሖዋ ክንድ ተማመኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • በጥልቅ ባሕር ውስጥ የሚኖሩ ግዙፍ ፍጥረታት
    ንቁ!—2009
  • ሮቦቶች ዛሬ ምን ደረጃ ላይ ደርሰዋል?
    ንቁ!—2008
  • የዝሆን ኩምቢ
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንድፍ አውጪ አለው?
ijwwd ርዕስ 3

ንድፍ አውጪ አለው?

አስደናቂው የኦክቶፐስ እጅ

የሮቦት ቴክኖሎጂ መሐንዲሶች፣ ሐኪሞች ሰውነትን በትንሹ ብቻ በመቅደድ ቀዶ ጥገና ለማድረግ የሚያስችላቸው መሣሪያ ለመሥራት እየሞከሩ ነው፤ በዚህ ዘዴ አማካኝነት ለቀዶ ጥገና አመቺ ያልሆኑ የሰውነት ክፍሎችን ማከም ይቻላል። በዚህ መስክ ለተደረሰበት አንድ የፈጠራ ሥራ አስተዋጽኦ ያደረገው፣ በከፍተኛ ሁኔታ መተጣጠፍ የሚችለው የኦክቶፐስ እጅ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ኦክቶፐስ እንደ ልብ መተጣጠፍ በሚችሉት ስምንት እጆቹ፣ ጠባብ በሆኑ ቦታዎች ውስጥም እንኳ ነገሮችን አፈፍ አድርጎ ማንሳት፣ መያዝ እንዲሁም ጭብጥ ማድረግ ይችላል። ኦክቶፐስ እጆቹን እንደፈለገው ማጠፍ ብቻ ሳይሆን የእጆቹን የተወሰኑ ክፍሎች እንደ አስፈላጊነቱ መገተርም ይችላል።

ተመራማሪዎች እንደ ኦክቶፐስ እጆች ለስላሳና በቀላሉ የሚተጣጠፍ የሮቦት እጅ፣ ሰውነትን በትንሹ ብቻ በመቅደድ የሚደረግ ቀዶ ሕክምና ለማካሄድ በጣም ጠቃሚ እንደሚሆን ያምናሉ። እንደዚህ ያለው መሣሪያ በጣም ውስብስብ ቀዶ ጥገና ለሚያስፈልጋቸው ሕመምተኞች በቀላሉ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ያስችላል።

በቀላሉ የሚተጣጠፉት የኦክቶፐስ እጆች ሲንቀሳቀሱ ተመልከት

ተመራማሪዎች እንደዚህ ዓይነት የሮቦት እጅ የሠሩ ሲሆን በቀዶ ጥገና ወቅት እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚያሳይ ሙከራም ተደርጓል። የዚህ ሮቦት አንዱ እጅ 135 ሚሊ ሜትር ሲሆን ለስላሳ የሆኑ የሰውነት ክፍሎችን ምንም ጉዳት ሳያደርስ በቀስታ አንስቶ መያዝ ይችላል፤ ሌላው እጅ ደግሞ ቀዶ ጥገናውን ያከናውናል። ይህን መሣሪያ የሠራው ቡድን አባል የሆኑት ዶክተር ቶማዞ ራንዛኒ “ይህ ዘዴ፣ ይበልጥ የተራቀቁ ገጽታዎች ላሏቸው አዲስና የተሻሻሉ መሣሪያዎች መነሻ ሊሆን እንደሚችል እናምናለን” ብለዋል።

ኦክቶፐስ እና የሮቦት እጅ

በቀላሉ መተጣጠፍ የሚችል ለስላሳ የሮቦት እጅ ለቀዶ ጥገና በጣም ጠቃሚ ይሆናል

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የኦክቶፐስ እጅ በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ