የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwwd ርዕስ 17
  • የሬሞራ መጣበቂያ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሬሞራ መጣበቂያ
  • ንድፍ አውጪ አለው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሻርክ ቆዳ
    ንቁ!—2010
  • የሻርክ ቆዳ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • የጥቃት ዒላማ የሆነው ነጩ ሻርክ
    ንቁ!—2000
  • በጥልቅ ባሕር ውስጥ የሚኖሩ ግዙፍ ፍጥረታት
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ንድፍ አውጪ አለው?
ijwwd ርዕስ 17
ሬሞራ ሲዋኝ። ከጭንቅላቱ በስተ ጀርባ ሞላላ ቅርጽ ያለው መጣበቂያ አለ።

ንድፍ አውጪ አለው?

የሬሞራ መጣበቂያ

ሬሞራ ሌሎች የባሕር ፍጥረታት ላይ የሚጣበቅ የዓሣ ዓይነት ነው፤ ይህ ዓሣ ሌሎች የባሕር ፍጥረታት ላይ ሙጭጭ ብሎ መጣበቅ ከዚያም የተጣበቀበትን ዓሣ ሳይጎዳ በቀላሉ መላቀቅ ይችላል። ይህ ችሎታው የተመራማሪዎችን ትኩረት ስቧል።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሬሞራ በሻርኮች፣ በባሕር ኤሊዎች፣ በዓሣ ነባሪዎች እንዲሁም የተለያየ ዓይነት ቆዳና ቅርፊት ባላቸው ሌሎች የባሕር ፍጥረታት ላይ ይጣበቃል። ሬሞራ ጥገኛ ተሕዋስያንንና የተጣበቀበት ዓሣ ያስተረፈውን ምግብ ይመገባል፤ በዚያ ላይ ደግሞ ዓሣው ላይ ተሳፍሮ ከቦታ ቦታ መጓጓዝና ከአዳኝ ዓሣዎች ጥበቃ ማግኘት ይችላል። ተመራማሪዎች ሬሞራ የተለያየ ዓይነት ቆዳና ቅርፊት ባላቸው ዓሦች ላይ ሙጭጭ ብሎ ሆኖም ጉዳት በማያደርስ መልኩ መጣበቅ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ስለ ሬሞራ መጣበቂያ እያጠኑ ነው።

በዓሣ ነባሪ ላይ የተጣበቁ ሬሞራዎች

የሬሞራ መጣበቂያ ሞላላ ቅርጽ ያለው ሲሆን የሚገኘውም ከጭንቅላቱ በስተ ጀርባ ነው። መጣበቂያው ዙሪያውን ለስላሳ ከንፈር ስላለው ዓሣው ላይ ሙጭጭ ብሎ መጣበቅ ይችላል። የመጣበቂያው መሃል ላይ ደግሞ መደዳውን የተደረደሩ ሸንተረሮች አሉ፤ በሸንተረሮቹ ላይ ጠንካራ የሆኑ ጥቃቅን አከርካሪዎች ይገኛሉ። ሸንተረሮቹ ቀጥ ብለው ሲቆሙ በሸንተረሮቹ ላይ ያሉት አከርካሪዎች ሬሞራው ከተጣበቀበት ዓሣ ቆዳ ጋር ይነካካሉ፤ ይህም በመጣበቂያውና በቆዳው መካከል ፍትጊያ ይፈጥራል። ይህ ፍትጊያ ሙጭጭ አድርጎ ከሚይዘው ከንፈር ጋር ሲደመር ሬሞራው በዓሣው ላይ በደንብ እንዲጣበቅ ያደርገዋል፤ በመሆኑም የተጣበቀበት ዓሣ በፍጥነት ቢዋኝም ሆነ በድንገት አቅጣጫውን ቢቀይር ሬሞራው ከዓሣው አይላቀቅም።

በሬሞራ መጣበቂያ የተገረሙት ተመራማሪዎች ተመሳሳይ የሆነ ሰው ሠራሽ መጣበቂያ ሠርተዋል። ሞላላ ቅርጽ ያለው ይህ መሣሪያ የተለያየ ተፈጥሮ ባላቸው ነገሮች ላይ መጣበቅ ይችላል። ተመራማሪዎቹ መሣሪያው ከራሱ ክብደት ብዙ መቶ እጥፍ የሚበልጥ ጉልበት ቢያርፍበትም እንኳ ሳይላቀቅ መቆየት እንደሚችል አረጋግጠዋል።

የሬሞራ መጣበቂያ ባለው ንድፍ ላይ የተመሠረተው ቴክኖሎጂ የተለያየ አገልግሎት ላይ ሊውል ይችላል። ለምሳሌ በባሕር ፍጥረታት ላይ ምልክት ለማድረግ፣ በጥልቅ ውቅያኖሶች ውስጥ ምርምር ለማድረግ እንዲሁም ውኃ ውስጥ ባለው የድልድይ ወይም የመርከብ ክፍል ላይ መብራትና ሌሎች መሣሪያዎችን ለማጣበቅ ሊያገለግል ይችላል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? የሬሞራ መጣበቂያ በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ