የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwwd ርዕስ 43
  • የእናት ጡት ወተት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የእናት ጡት ወተት
  • ንድፍ አውጪ አለው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የእናት ጡት ወተት የሚመረጥበት ምክንያት
    ንቁ!—1994
  • የወተት ማለፊያ ቧንቧ
    ንቁ!—2008
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • “የእውነትን ቃል በትክክል የሚጠቀም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ንድፍ አውጪ አለው?
ijwwd ርዕስ 43
አንዲት እናት እቅፏ ውስጥ የተኛውን ልጇን እያየች።

ንድፍ አውጪ አለው?

የእናት ጡት ወተት

ለአዋላጆች የተዘጋጀ አንድ መጽሐፍ እንደሚገልጸው “ለጨቅላ ሕፃናት የተዘጋጀ የዱቄት ወተት የእናት ጡት ወተትን ፈጽሞ ሊተካ አይችልም።” የእናት ጡት ወተት ለልጇ ከሁሉ የተሻለ የሆነበት አንዱ ምክንያት ሰውነቷ ሕፃኑ የሚያስፈልገውን ነገር ከግምት በማስገባት የወተቱን ይዘት የሚቀያይረው መሆኑ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ አንዲት እናት ልጇን በምታጠባበት በእያንዳንዱ ጊዜ ሕፃኑ መጥባቱን ጀምሮ እስኪጨርስ ድረስ የወተቱ ይዘት ይቀያየራል። ሕፃኑ መጥባት እንደጀመረ የሚወጣው ወተት ብዙ ፕሮቲን፣ ቫይታሚን፣ ማዕድንና ውኃ አለው፤ ወደ መጨረሻ አካባቢ የሚወጣው ወተት ደግሞ ቅባታማ ነው፤ ይህም ሕፃኑ እንዲጠግብ ያደርገዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የእናት ጡት ወተት የሕፃኑን ዕድሜና ወቅቱን መሠረት በማድረግ ይቀያየራል።

ምሽት ላይ የሚመነጨው የእናት ጡት ወተት እንቅልፍ የሚያመጣ ሆርሞን የሆነውን ሜላቶኒንን ጨምሮ አንዳንድ ሆርሞኖችን በብዛት ይይዛል፤ ቀን ላይ ደግሞ የሌሎች ሆርሞኖች መጠን ይጨምራል። በዚህ መንገድ በቀኑ ውስጥ የሆርሞኖቹ መጠን መቀያየሩ ሕፃኑ የተወሰነ ሰዓት ላይ እንዲተኛ፣ የተወሰነ ሰዓት ላይ ደግሞ እንዲነቃ ይረዳዋል።

እናትየው ከወለደች በኋላ ባሉት የመጀመሪያ ጥቂት ቀናት ወደ ቢጫ የሚጠጋ ቀለም ያለው እንገር ታመነጫለች። እንገር ለመፈጨት ቀላል ከመሆኑም ሌላ ብዙ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፤ በመሆኑም ትንሽ በሆነው የአራሱ ሆድ ውስጥ የሚገባ ጥቂት እንገር እንኳ ብዙ ጥቅም ያስገኝለታል። አራሱ ለበሽታ ተጋላጭ ቢሆንም እንኳ እንገር በሽታ ለመከላከል የሚረዱ በርካታ ንጥረ ነገሮችን ይሰጠዋል። ከዚህም በተጨማሪ እንገር ሕፃኑ እንዲጸዳዳ ስለሚረዳው ሆድ ዕቃውን ያጸዳለታል።

እናቶች መንታ ቢወልዱም እንኳ ‘በቂ ወተት ይኖረኛል ወይ’ ብለው መስጋት አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም የወተት አቅርቦቱ እንደ አስፈላጊነቱ ይጨምራል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? አስደናቂ የሆነው የእናት ጡት ወተት በዝግመተ ለውጥ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ