በሕፃናት ላይ የሚፈጸመውን የጭካኔ ተግባር መከላከል፣ 1882
“በሕፃናት ላይ የሚፈጸመውን የጭካኔ ተግባር ለመከላከል የተቋቋመ ማኅበር፣ 1882። በሕፃናት ላይ የሚፈጸመውን የጭካኔ ተግባር የሚከላከለው ማኅበር የተቋቋመው በ1875 በኒው ዮርክ ከተማ ሲሆን ያቋቋመውም ሄንሪ በርግ የተባለ ሰው ነበር። ማኅበሩ ከተቋቋመ ከሰባት ዓመት በኋላ በከተማው ውስጥ ጭከና ለሚፈጸምባቸው ሕፃናት ማንኛውንም ጥበቃ የሚያደርግ የመጀመሪያው ድርጅት ሆነ። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አቤቱታዎችን ይሰማ፣ ልጆችን ምቹ ካልሆኑ መኖሪያ ቤቶች ያወጣና ጥፋተኞቹን በፍርድ ቤት ከስሶ ሕግ ፊት ያቀርብ ነበር። ይህ ስሜት የሚነካ ሥዕላዊ መግለጫ በወቅቱ የነበሩት ባለ ሥልጣኖች በአንድ ቤት ውስጥ ያደርጉት የነበረውን የገላጋይነት ተግባር ያሳያል።”—ኒው ዮርክ በአሥራ ዘጠነኛው ዘመን፤ (ኒው ዮርክ ኢን ዘ ናይንቲንዝ ሴንቸሪ) በጆን ግራፍተን የተጻፈ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ምንጭ]
New York in the Nineteenth Century, by john Grafton, Dover Publications, Inc.