የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g95 4/8 ገጽ 12
  • ያንኮራፋሉን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ያንኮራፋሉን?
  • ንቁ!—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከባድ የሆኑ የእንቅልፍ በሽታዎችን መለየት
    ንቁ!—2004
  • የልጆች እንቅልፋምነት አሳሳቢ ችግር ሆኗልን?
    ንቁ!—2002
  • ጥሩ እንቅልፍ መተኛት የሚቻለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2003
  • በጭንቀት ምክንያት የሚመጣ የስሜት ቀውስ ያለባቸውን ሰዎች መርዳት
    ንቁ!—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1995
g95 4/8 ገጽ 12

ያንኮራፋሉን?

እንቅልፍ ሲወስደዎት በጣም ያንኮራፋሉን? አንዳንድ ሰዎች በጣም ያንኮራፋሉ። ቢሆንም የሚያንኮራፉ መሆናቸውን እንኳ አያውቁም። በዚህም ምክንያት ጠዋት ሲነሱ የድካምና የመጫጫን ስሜት ለምን እንደሚሰማቸው አያውቁም። የእነዚህ ሰዎች ችግር በእንግሊዝኛ ስሊፕ አፕኒያ ተብሎ ይጠራል። ይህ ዓይነቱ ችግር ያለበት ሰው በሚተኛበት ጊዜ የእስትንፋስ መተላለፊያዎች ክፍት እንዲሆኑ የሚያደርጉት ጡንቻዎች ከመጠን በላይ ስለሚለጠጡ የትንፋሽ መተላለፊያው ይዘጋል። ሰውዬው አየር አጥሮት ከእንቅልፉ እስኪባንን ድረስ አንድ ደቂቃ የሚያህል ጊዜ ሊያልፍ ይችላል። የአፕኒያ ችግር ካለባቸው ሰዎች አብዛኞቹ እንቅልፋቸው የተረበሸ መሆኑ አይታወቃቸውም። ብዙውን ጊዜ በማንኮራፋታቸው እንቅልፍ አጥቶ የተቸገረ አብሯቸው የሚተኛ ሰው ካልነገራቸው በቀር ስለ ማንኮራፋታቸው አያውቁም። ሊቃውንት አፕኒያ በመኪናም ሆነ በሥራ ቦታ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች፣ እንዲሁም ለልብ ድካምና በደም ግፊት ብዛት ምክንያት ለሚደርስ ሽባነት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ያምናሉ።

ታዲያ ይህ ችግር መፍትሔ ይኖረዋልን? ዘ ኮምፕሊት ሆም ሜዲካል ጋይድ (የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሐኪሞችና ሰርጀኖች ኮሌጅ ጽሑፍ) የተባለው መጽሐፍ እንደሚከተለው በማለት ይመክራል:- “በዚህ ችግር የሚጠቁት ወንዶች ቁጥር ከሴቶቹ በ20 እጥፍ ይበልጣል። ከሚያንኮራፉ ሰዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወፍራሞች ናቸው። ውፍረት ራሱ የአየር መተላለፍ ችግር ያስከትላል። ስለዚህ ክብደት መቀነስ አንዱ አስፈላጊ የሆነ የሕክምና ክፍል ነው።” ይኸው መጽሐፍ ችግሩ ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ የአየር መተላለፊያ ቧንቧዎችን ለመክፈት የሚያስችል ቀዶ ሕክምና ማድረግ ጥሩ ሊሆን እንደሚችል ሐሳብ ይሰጣል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ