የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/11 ገጽ 20-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2011
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነት ምንድን ነው?
  • ካርድ በመሰብሰብ መማር
  • ሕዝቦችና አገሮች
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2011
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 12/11 ገጽ 20-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነት ምንድን ነው?

በሥዕል ሀ እና በሥዕል ለ መካከል ያሉትን ሦስት ልዩነቶች መናገር ትችላለህ? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

ፍንጭ፦ ኢሳይያስ 6:1-8⁠ን አንብብ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

4. ትክክለኛው ሥዕል የትኛው ነው? ሥዕል ሀ ነው ወይስ ሥዕል ለ?

ለውይይት፦

ኢሳይያስ ምን ጥሩ ዝንባሌ ነበረው? አንተስ ትሑት እንደሆንክና የፈቃደኝነት መንፈስ እንዳለህ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ መዝሙር 110:3⁠ን እና ማቴዎስ 28:19, 20⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

እያንዳንዱ የቤተሰባችሁ አባል ስለ መላእክት የሥራ ድርሻ ለማወቅ ምርምር ያድርግ። ከዚያም አንድ ላይ ተሰብሰቡና ምን እንዳገኛችሁ ተነጋገሩ። ለምሳሌ ያህል፣ መላእክት ከሚያከናውኗቸው ሥራዎች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?

ፍንጭ፦ መዝሙር 34:7⁠ን፤ ዕብራውያን 1:14⁠ን እና ራእይ 14:6, 7⁠ን አንብብ።

መላእክት የተደራጁ ናቸው?

ፍንጭ፦ መዝሙር 103:19-21⁠ን አንብብ።

መላእክት ትሑቶችና ሌሎችን ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው?

ፍንጭ፦ መሳፍንት 13:17, 18⁠ን፤ ሉቃስ 22:43⁠ን እና ራእይ 22:8, 9⁠ን አንብብ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 12 ኢሳይያስ

ጥያቄ

ሀ. ለንጉሥ አካዝ መልእክት ለማድረስ ከኢሳይያስ ጋር የሄደው ማን ነው?

ለ. ይሖዋ “ማንን እልካለሁ?” ብሎ ሲጠይቅ ኢሳይያስ ምን ምላሽ ሰጠ?

ሐ. ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ተንብዮ ነበር፦ “ምድር ሁሉ . . . ”

[ሰንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

ኢሳይያስ የኖረበት ዘመን 700 ዓ.ም. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

በኢየሩሳሌም ኖሯል

ኢየሩሳሌም

ኢሳይያስ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ቤተሰቡ አምላክን እንዲያመልክ ጥረት ያደረገ ታማኝ ነቢይ ነው። የተሰጠውን ተልእኮ በሚገባ በመወጣት ለቤተሰቡ ጥሩ አርዓያ ሆኗል። ሚስቱ “ነቢዪቱ” ተብላ ተጠርታለች። (ኢሳይያስ 7:3፤ 8:3, 18) ኢሳይያስ ቢያንስ ለ46 ዓመታት አምላክን አገልግሏል። ስሙ “የይሖዋ ማዳን” የሚል ትርጉም አለው።

መልስ

ሀ. ልጁ ሸአር ያሹብ።​—ኢሳይያስ 7:3

ለ. “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ።”​—ኢሳይያስ 6:8

ሐ. “. . . እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለች።”​—ኢሳይያስ 11:9

ሕዝቦችና አገሮች

5. አቢግያ እና ይሪያ እንባላለን፤ የ9 እና የ7 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በሕንድ ነው። በሕንድ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 31,500፣ 59,600 ወይስ 86,000?

6. የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከሕንድ በጣም ይርቃል?

ሀ

ለ

ሐ

መ

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.pr2711.com ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 20 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. መልአኩ በአንደኛው ሥዕል ላይ ያሉት ክንፎች ስድስት ሲሆኑ በሌላኛው ላይ ግን አራት ናቸው።

2. መልአኩ በአንደኛው ሥዕል ላይ የያዘው ጉጠት ወይም መቆንጠጫ ሲሆን በሌላኛው ሥዕል ላይ ግን ሰይፍ ነው።

3. በአንደኛው ሥዕል ላይ ፍሙ የነካው የኢሳይያስን ከንፈሮች ሲሆን በሌላኛው ሥዕል ላይ ግን ፍሙ የነካው እጆቹን ነው።

4. ለ

5. 31,500

6. ለ

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

La Voz de Galicia/Fotógrafo: Víctor Mejuto

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ