የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/12 ገጽ 16-18
  • ወንድነት የሚለካው በምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወንድነት የሚለካው በምንድን ነው?
  • ንቁ!—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ዕድገታችሁ በግልጽ ይታይ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ከወንድ ልጅህ ጋር ያለህ ጓደኝነት እንዲቀጥል ምን ማድረግ ትችላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ቅርርባችን ከተራ ጓደኝነት ያለፈ ነው? ክፍል 2
    ንቁ!—2012
  • ይህ ሰው ይሆነኛል?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2012
g 12/12 ገጽ 16-18

የወጣቶች ጥያቄ

ወንድነት የሚለካው በምንድን ነው?

“አባቴ የሞተው የሦስት ዓመት ልጅ ሳለሁ ነበር። አባታቸው ያሳደጋቸውን ልጆች ሳይ አንዳንድ ጊዜ እቀናለሁ። ከእኔ የተሻለ በራስ የመተማመን ስሜት እንዳላቸው ይሰማኛል።”—አሌክስa

“ከአባቴ ጋር ብዙ አንቀራረብም። በመሆኑም ወንድ መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ያወቅኩት በራሴ ጥረት ነው።”—ጆናታን

ከላይ እንደተጠቀሱት ወጣቶች ተሰምቶህ ያውቃል? ወንድነት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ በትክክል ማወቅ አለመቻል ያሳስብሃል? ከሆነ ሐሳብ አይግባህ!

ሁለት የተለመዱ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን እንዴት ማሸነፍ እንደምትችል እስቲ እንመልከት።

ተፈታታኝ ሁኔታ 1፦ ብዙዎች ያላቸው የተሳሳተ አመለካከት

አንዳንዶች ምን ይላሉ?

  • ወንድ ልጅ ጠንካራ መሆን አለበት፤ ፈጽሞ ማልቀስ የለበትም።

  • ወንድ ልጅ ማንም እንዲህ አድርግ እንዲለው መፍቀድ የለበትም።

  • ወንዶች ከሴቶች ይበልጣሉ።

ጉዳዩ ከሌላ አቅጣጫ ሲታይ፦ አንድ ወንድ፣ ሙሉ ሰው ሲሆን ልጅ ከነበረበት ጊዜ የተሻለ ብስለት ይኖረዋል፤ ይህ ሲባል ግን ከሴቶች የሚበልጥ ይሆናል ማለት አይደለም። የወንድነት ባሕርይ አለህ የሚባለው የልጅነት ባሕርይህን ስትተው ነው። ክርስቲያኑ ሐዋርያው ጳውሎስ የሚከተለውን ጽፏል፦ “ሕፃን በነበርኩበት ጊዜ እንደ ሕፃን እናገር፣ እንደ ሕፃን አስብ እንዲሁም እንደ ሕፃን አመዛዝን ነበር፤ አሁን ሙሉ ሰው ከሆንኩ በኋላ ግን የሕፃንነትን ጠባይ ትቻለሁ።” (1 ቆሮንቶስ 13:11) በሌላ አነጋገር የልጅነት አስተሳሰብ፣ አነጋገርና ምግባር ትተህ ብስለት የሚንጸባረቅበት አስተሳሰብ፣ አነጋገርና ምግባር እያዳበርክ ስትሄድ ሙሉ ሰው ወይም ወንድ መባል ትችላለህ።b

እንዲህ ለማድረግ ሞክር፦ ቀጥሎ ለቀረቡት ጥያቄዎች የምትሰጠውን መልስ በወረቀት ላይ አስፍር፦

  1. “የሕፃንነትን ጠባይ” በመተው ረገድ በየትኞቹ ነገሮች ተሳክቶልኛል?

  2. የትኞቹን ነገሮችስ ማሻሻል ይገባኛል?

በተጨማሪም ሉቃስ 7:36-50⁠ን አንብብ። ኢየሱስ (1) ትክክል ለሆነው ነገር አቋም በመውሰድ እንዲሁም (2) ሴቶችን ጨምሮ ሌሎችን በአክብሮት በመያዝ ትክክለኛ የወንድነት ባሕርይ ያሳየው እንዴት እንደሆነ ልብ በል።

“ጓደኛዬን ኬንን አደንቀዋለሁ። አካላዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ ጥንካሬ አለው፤ እንዲሁም ደግ ሰው ነው። የእሱ ምሳሌነት ትክክለኛ የወንድነት ባሕርይ ያለው ሰው ራሱን ከፍ ለማድረግ ሲል ሌሎችን ዝቅ እንደማያደርግ እንድገነዘብ ረድቶኛል።”—ጆናታን

ተፈታታኝ ሁኔታ 2፦ ጥሩ ምሳሌ የሚሆን አባት አለማግኘት

አንዳንዶች ምን ይላሉ?

  • ከአባትህ ጋር የማትኖር ከሆነ ወንድነት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ፈጽሞ ማወቅ አትችልም።

  • አባትህ መጥፎ ምሳሌ ከሆነ አንተም እሱ የሚሠራቸውን ስህተቶች መድገምህ አይቀርም።

ጉዳዩ ከሌላ አቅጣጫ ሲታይ፦ አስተዳደግህ ያን ያህል ጥሩ ባይሆንም እንኳ ትክክለኛ የወንድነት ባሕርያትን ማዳበር አትችልም ማለት አይደለም! ያለህበትን ሁኔታ መቀየር ትችላለህ። (2 ቆሮንቶስ 10:4) ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰለሞን የሰጠውን “በርታ፤ ቆራጥ ወንድ ሁን” የሚለውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ትችላለህ።—1 ነገሥት 2:2 NW

እርግጥ ነው፣ ለልጁ እምብዛም ትኩረት ከማይሰጥ አባት ጋር መኖር ወይም እስከ ጭራሹ ያለ አባት ማደግ ከባድ ነው። በዚህ ርዕስ መግቢያ ላይ የተጠቀሰው አሌክስ “አባትን አለማወቅ በጣም ይጎዳል” ብሏል። “አሁን 25 ዓመቴ ሲሆን በአሥራዎቹ ዕድሜ እያለሁ መማር የነበረብኝን ነገሮች ገና እያወቅሁ እንዳለሁ ይሰማኛል።” አንተም እንደ አሌክስ የሚሰማህ ከሆነ ምን ማድረግ ትችላለህ?

እንዲህ ለማድረግ ሞክር፦ እንደ አባት መካሪ ሊሆንልህ የሚችል ጥሩ አርዓያ የሚሆን ሰው ፈልግ።c አንድ ወንድ ሊያዳብራቸው የሚገቡ ትክክለኛ ባሕርያት የትኞቹ እንደሆኑ ጠይቀው። ከዚያም አንተ እነዚህን ባሕርያት ማዳበር የምትችለው እንዴት እንደሆነ ጠይቀው።—ምሳሌ 1:5

በተጨማሪም ምሳሌ መጽሐፍ ከምዕራፍ 1 እስከ 9 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ አንብብ። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የሚገኘውን አንድ ልጅ ጥበበኛና መንፈሳዊ መሆን እንዲችል የሚረዳ አባታዊ ምክር ልብ በል።

“ትክክለኛ የወንድ ባሕርያትን እያዳበርኩ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ። በእርግጥ እንዲህ ያለ እድገት ሳደርግ አባቴ ቢረዳኝ ደስ ይለኝ ነበር፤ ያም ባይሆን ግን ወደፊት የተሻለ ሰው መሆን እንደምችል ይሰማኛል። ትክክለኛ የወንድነት ባሕርያትን ማዳበር እንደምችል እርግጠኛ ነኝ!”—ጆናታን

ከጥር 2013 የንቁ! እትም ጀምሮ “የወጣቶች ጥያቄ” በሚለው ዓምድ ሥር የሚወጡት ርዕሶች የሚገኙት

a በዚህ ርዕስ ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።

b “ልጅና ሙሉ ሰው ሲነጻጸር” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።

c በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ የሚገኙ ሽማግሌዎች ጥሩ መካሪ ሊሆኑ ይችላሉ።

ኢየን—ወንድ መሆን ሲባል የወንድነት ባሕርያት ማሳየት ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ሠራተኛ መሆንን፣ ስሜትን መቆጣጠርን እንዲሁም ለምታደርጋቸው ነገሮች ኃላፊነት መውሰድን ያጠቃልላል።

ልጅና ሙሉ ሰው ሲነጻጸር

አብዛኛውን ጊዜ በልጆች ላይ የሚታዩ ባሕርያት . . .

  • ሰው አለማክበር

  • ራስ ወዳድ መሆን

  • ጨዋታ ላይ ብቻ ማተኮር

  • በስሜት መነዳት

ሙሉ ሰው ለማዳበር የሚፈልጋቸው ባሕርያት . . .

  • ሰው ማክበር—ሮም 12:10

  • የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ—1 ቆሮንቶስ 10:24

  • ኃላፊነት የሚሰማው መሆን—ገላትያ 6:5

  • ስሜትን መቆጣጠር—ምሳሌ 16:32

ወላጆችህን ለምን አትጠይቃቸውም?

የወንድነት መገለጫው ምን ይመስላችኋል? ብስለት በማሳየት ረገድ እኔ እንዴት ነኝ?

ለወላጆች የቀረበ ሐሳብ

አባቶች—

ወንድ ልጅህ፣ ወንድነት ምን ማለት እንደሆነ የሚለካው በአብዛኛው የአንተን ባሕርይ በመመልከት ነው። ሚስትህን በአክብሮት የምትይዝ ከሆነ ሴቶችን በአክብሮት መያዝ እንዳለበት እያስተማርከው ነው። ለቤተሰብህ የሚያስፈልገውን ለማቅረብ ዝቅ ተደርጎ የሚታይ ወይም አድካሚ ሥራ መሥራት ቢኖርብህም እንኳ ጠንክረህ የምትሠራ ከሆነ ታታሪ ሠራተኛ እና ኃላፊነት የሚሰማው ሰው እንዲሆን እያሠለጠንከው ነው።—1 ጢሞቴዎስ 5:8

ምናልባት ከአባትህ ጋር ጥሩ ግንኙነት አልነበረህ ይሆናል። አባትህም እንዲሁ ከአባቱ ጋር ጥሩ ግንኙነት አልነበረው ይሆናል። ያም ቢሆን በአንተና በልጅህ መካከል ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ማድረግ ትችላለህ። ይህን ማድረግ የምትችልበት አጋጣሚ አያምልጥህ! ከወንድ ልጅህ ጋር ለመቀራረብ ጥረት አድርግ።d ጥሩ ምሳሌ ሁንለት፤ እንዲህ ካደረግህ ሲያድግ የምትኮራበትና ግሩም ባሕርያት ያሉት ሰው ይሆናል።—ምሳሌ 23:24

እናቶች—

ወንድ ልጅሽ ግሩም የሆኑ የወንድ ባሕርያትን ማዳበር እንዲችል ልትረጂው የምትችይው እንዴት ነው? ልጅሽን ከባልሽ ጋር አታወዳድሪው። ለምሳሌ ያህል፣ ልጅሽ ባልሽ ይሠራው የነበረውን ዓይነት ስህተት ፈጸመ እንበል። በዚህ ጊዜ “ልክ እንዳባትህ እየሆንክ ነው!” ብለሽ ለመናገር ትፈተኚ ይሆናል። ልጅሽ ስህተት ሲሠራ እርማት መስጠትሽ ትክክል እንደሆነ ጥያቄ የለውም። ይሁን እንጂ ንግግርሽ ወይም ድርጊትሽ ባልሽ የሚሠራው ነገር ሁሉ ስህተት እንደሆነ የሚጠቁም ከሆነ ልጅሽ የወንድነትን ባሕርያት ማዳበር አስቸጋሪ እንዲሆንበት ታደርጊያለሽ።

ባልሽ ከልጃችሁ እድገት ጋር በተያያዘ የሚያበረክተውን ድርሻ ለመደገፍ ጥረት አድርጊ። አብረው ጊዜ እንዲያሳልፉ አበረታቻቸው፤ እንዲሁም ባገኘሽው አጋጣሚ ተጠቅመሽ የባልሽን መልካም ባሕርያትና የሚያደርጋቸውን ጥሩ ነገሮች ለልጅሽ ንገሪው። ባልሽ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ነገር ለማቅረብ ጠንክሮ ይሠራል? ከልጆቹ ጋር ጊዜ ያሳልፋል? ሌሎችን በአክብሮት ይይዛል? እነዚህን ባሕርያቱን እንደምታደንቂለት ለልጅሽ ግለጪለት። እንዲህ ማድረግሽ ልጅሽ፣ የአባቱን አርዓያ እንዲከተል ይረዳዋል።

d ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች በሚዘጋጀው መጠበቂያ ግንብ መጽሔት የኅዳር 1, 2011 እትም ላይ የወጣውን “ከወንድ ልጅህ ጋር ያለህ ጓደኝነት እንዲቀጥል ምን ማድረግ ትችላለህ?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ