የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 12/15 ገጽ 14
  • የዜናው ትኩረት—አውሮፓ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የዜናው ትኩረት—አውሮፓ
  • ንቁ!—2015
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የእናት ድምፅ ያሉት ጥቅሞች
  • ራስ ወዳድነትን ማበረታታት
  • አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው የዕድሜ ባለጸጎች
  • ረጅም ዕድሜ የመኖር ሚስጥር በኦኪናዋ ተገኝቶ ይሆን?
    ንቁ!—2008
  • ራስ ወዳድ በሆነ ዓለም ውስጥ ጨዋ ልጆች ማሳደግ
    ንቁ!—2013
  • ሕፃናት የሚያስፈልጋቸውና የሚፈልጉት
    ንቁ!—2004
  • የወላጅነት የሥራ ድርሻ
    ንቁ!—2004
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2015
g 12/15 ገጽ 14
አንዲት እናት ልጇን ስታናግር

ከዓለም አካባቢ

የዜናው ትኩረት—አውሮፓ

በአንድ ወቅት በጣም ሃይማኖተኛ የነበሩት የአውሮፓ ነዋሪዎች አሁን በአብዛኛው ለሃይማኖት ግድ የለሽ ሆነዋል። ይሁንና በቅርቡ ከአውሮፓ የተሰሙ ዜናዎች በሚያስገርም ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ የሚደግፉ ናቸው።

የእናት ድምፅ ያሉት ጥቅሞች

በሚላን፣ ጣሊያን ያሉ ተመራማሪዎች አለጊዜያቸው የተወለዱ ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ልጆች እጃቸው ላይ በሚደረግ መሣሪያ አማካኝነት የእናታቸውን ድምፅ መስማታቸው ለጤንነታቸው ብዙ ጥቅም እንዳለው ደርሰውበታል። ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት ሕፃኑ በእናቱ ማህፀን ውስጥ ቢሆን ኖሮ ድምጿን የሚሰማበትን መንገድ በማስመሰል የተሠራ ነው። ጥናቱ እንደደረሰበት ከሆነ “ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ ሕፃናት የእናታቸውን ድምፅ እንዲሰሙ መደረጉ ጥሩ ውጤት ያመጣል።”

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “እናቱ ላይ እንደተቀመጠ ጡት የጣለ ሕፃን ነፍሴን አረጋጋኋት፤ ደግሞም ጸጥ አሰኘኋት።”—መዝሙር 131:2

ራስ ወዳድነትን ማበረታታት

ኔዘርላንድ ውስጥ በ565 ልጆች ላይ የተደረገ ጥናት እንዳሳየው ወላጆቻቸው “ከሌሎች ልጆች የተለያችሁ ናችሁ” የሚሏቸውና “ልዩ እንክብካቤ” እንደሚገባቸው የሚነግሯቸው ልጆች ከእኩዮቻቸው የበለጠ ራስ ወዳዶች ይሆናሉ፤ እንዲሁም ከሌሎች የተሻሉ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። የዚህ ጥናት አዘጋጅ እንደተናገሩት “ልጆች ከሌሎች እንደሚበልጡ ወላጆቻቸው ሲነግሯቸው ያምኗቸዋል፤ ይህ ደግሞ ለራሳቸውም ሆነ ለማኅበረሰቡ ጎጂ ሊሆን ይችላል።”

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “እያንዳንዱ ሰው ከሚገባው በላይ ስለ ራሱ በማሰብ ራሱን ከፍ አድርጎ አይመልከት፤ ከዚህ ይልቅ . . . ጤናማ አስተሳሰብ እንዳለው በሚያሳይ መንገድ [ያስብ]።”—ሮም 12:3

አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው የዕድሜ ባለጸጎች

መቶ ዓመት የሞላቸው የዕድሜ ባለጸጎች የአቅም ውስንነትና ሕመም ቢኖርባቸውም በሕይወት የመቀጠል ፍላጎታቸው ከፍተኛ እንደሆነ ጀርመን ውስጥ ያለው የሃይድልቤርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ገለጹ። ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው የዕድሜ ባለጸጎች መካከል በአማካይ ከአራቱ ሦስቱ በሕይወት መኖርን የሚወዱ ከመሆኑም ሌላ ደስተኛ ለመሆን የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ። እነዚህ ሰዎች ያወጧቸው ግቦች ላይ መድረስ ችለዋል፤ አዎንታዊ አመለካከትና ብሩህ ተስፋ አላቸው፤ ሕይወት ትርጉም እንዳለው ይሰማቸዋል፤ እንዲሁም በጥብቅ የሚከተሏቸው ሃይማኖታዊና ሥነ ምግባራዊ እሴቶች አሏቸው።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ በመክብብ 3:11 ላይ እንደተገለጸው የሰው ልጆች በሕይወት የመኖር ተፈጥሯዊ ፍላጎት ያላቸው መሆኑ ምን ያሳያል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ