ለቤተሰቦች የሚሆን ተጨማሪ እርዳታ
መጽሐፍ ቅዱስ ለባለትዳሮች፣ ለወላጆችና ለወጣቶች አስተማማኝ መመሪያ ይሰጣል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት መመሪያዎች አንድ ሰው ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ እንዲኖረው ይረዳሉ።—ምሳሌ 1:1-4
በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ለሚከተሉት አንገብጋቢ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፦
የሕይወት ትርጉም ምንድን ነው?
ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂው አምላክ ነው?
ስንሞት ምን እንሆናለን?
የእነዚህንና የሌሎች ጥያቄዎችን መልስ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን እንድትመረምር እንጋብዝሃለን። መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት። www.pr2711.com/amን መጎብኘት ትችላለህ።