የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g21 ቁጥር 2 ገጽ 13-15
  • ቴክኖሎጂ የሚያሳድረው ተጽዕኖ—​በአስተሳሰብህ ላይ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቴክኖሎጂ የሚያሳድረው ተጽዕኖ—​በአስተሳሰብህ ላይ
  • ንቁ!—2021
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማወቅ የሚኖርብህ ነገር
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር መሥራት ጠቃሚ ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ቴክኖሎጂ ሕይወታችንን እንዳይቆጣጠረው ማድረግ
    ለቤተሰብ
  • ቴክኖሎጂን በአሳቢነትና በቁጠባ ተጠቀሙበት
    ንቁ!—2009
  • ትኩረቴን መሰብሰብ የምችለው እንዴት ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2021
g21 ቁጥር 2 ገጽ 13-15
አንድ ሰው የምግብ አሠራርን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን እየተመለከተ ምግብ ሲሠራ።

ቴክኖሎጂ የሚያሳድረው ተጽዕኖ—​በአስተሳሰብህ ላይ

ሰዎች በትምህርት፣ በሥራ ወይም በሌሎች ምክንያቶች እውቀት መቅሰም ያስፈልጋቸዋል። ቴክኖሎጂ በዚህ ረገድ ትልቅ እገዛ ያበረክታል። የተለያዩ መረጃዎችን ማግኘት የአሁኑን ጊዜ ያህል ቀላል ሆኖ አያውቅም። ከቤታችን መውጣት፣ ሌላው ቀርቶ ከወንበራችን መነሳት እንኳ ሳያስፈልገን ብዙ መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን።

ይሁንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በስፋት የሚጠቀሙ በርካታ ሰዎች የሚከተሉት ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፦

  • ሲያነብቡ በቀላሉ ትኩረታቸው ይከፋፈላል።

  • አንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ለመሥራት ይቸገራሉ።

  • ብቻቸውን ሲሆኑ ቶሎ ይሰላቻሉ።

ማወቅ የሚኖርብህ ነገር

በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የምትገኝ አንዲት ልጅ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ስታደርግ። ስልኳ ላይ መልእክት እየጻፈች፣ ከጓደኛዋ ጋር በቪዲዮ እየተነጋገረች እንዲሁም ኮምፒውተሯንና መጽሐፍ ተጠቅማ እያጠናች ነው።

ንባብ

አንዳንዶች ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ ትዕግሥቱ ስለሌላቸው አለፍ አለፍ እያሉ ማንበብን ይመርጣሉ።

እንዲህ ያለው ንባብ ለአንድ ጥያቄ ቶሎ መልስ ማግኘት ስንፈልግ ይጠቅመናል። ሆኖም አንድን ርዕሰ ጉዳይ በጥልቀት መረዳት የምንፈልግ ከሆነ ይህ ዘዴ አያዋጣንም።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ረዘም ያሉ ጽሑፎችን ለማንበብ ትቸገራለህ? ሙሉውን ጽሑፍ በትዕግሥት ማንበብህ ከምታነበው ነገር የተሻለ ጥቅም ለማግኘት የሚረዳህ እንዴት ነው?—ምሳሌ 18:15

ትኩረትን መሰብሰብ

አንዳንድ ሰዎች ቴክኖሎጂ ሁለት ነገሮችን በተመሳሳይ ጊዜ ላይ ለመሥራት እንደሚያስችላቸው፣ ለምሳሌ እያጠኑ ለጓደኞቻቸው የጽሑፍ መልእክት መላክ እንደሚችሉ ይሰማቸዋል። ይሁንና እነዚህ ሰዎች ትኩረታቸው ስለሚከፋፈል ሁለቱንም ነገሮች በአግባቡ ማከናወን ሊከብዳቸው ይችላል።

ትኩረትን መሰብሰብ ራስን መገሠጽን ይጠይቃል፤ ሆኖም በዚህ ረገድ የምናደርገው ጥረት አያስቆጭም። ግሬስ የተባለች ወጣት ትኩረትን መሰብሰብ “ብዙ ስህተት ላለመሥራትና ውጥረትን ለመቀነስ እንደሚረዳ” ተናግራለች። አክላም “የተለያዩ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ለመሥራት ከመሞከር ይልቅ በአንድ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ የተሻለ እንደሆነ አስተውያለሁ” ብላለች።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ የተለያዩ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ለማከናወን በመሞከርህ ምክንያት የምታነበውን ነገር ለመረዳትና ለማስታወስ ትቸገራለህ?—ምሳሌ 17:24

ለብቻ መሆን

አንዳንድ ሰዎች ብቻቸውን መሆን ስለሚጨንቃቸው ዘና ለማለት የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይጠቀማሉ። ኦሊቪያ የተባለች ሴት “ስልኬን ወይም ታብሌቴን ሳልከፍት ወይም ቴሌቪዥን ሳላይ 15 ደቂቃ ከቆየሁ ይሰለቸኛል” በማለት ተናግራለች።

ይሁንና አልፎ አልፎ ብቻችንን መሆናችን ስለ አንዳንድ ጉዳዮች በጥልቀት የምናስብበት አጋጣሚ ይሰጠናል፤ ልጆችም ሆኑ አዋቂዎች ትምህርት መቅሰም ከፈለጉ እንዲህ የሚያደርጉበት ጊዜ መመደባቸው በጣም አስፈላጊ ነው።

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ብቻህን የምትሆንበትን ጊዜ ስለ አንዳንድ ነገሮች በጥልቀት ለማሰብ ትጠቀምበታለህ?—1 ጢሞቴዎስ 4:15

ምን ማድረግ ትችላለህ?

የቴክኖሎጂ አጠቃቀምህን ገምግም

የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ትምህርት ለመቅሰም ልትጠቀምባቸው የምትችለው እንዴት ነው? ቴክኖሎጂ ትኩረትህን መሰብሰብና መማር ከባድ እንዲሆንብህ ሊያደርግ የሚችለውስ እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ጥበብንና የማመዛዘን ችሎታን ጠብቅ።”—ምሳሌ 3:21

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ላይ ረዘም ያለ ነገር ሳነብ ትኩረቴን መሰብሰብ ይከብደኛል? ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ ትኩረቴን የሚከፋፍለው ነገር ምንድን ነው?

  • ትኩረቴን የሚከፋፍሉትን ነገሮች ለመቀነስ ብሎም ለማስወገድ ምን እርምጃዎች መውሰድ እችላለሁ?

ጠቃሚ ምክር፦ አጠር አጠር ያሉ ክፍሎችን በማንበብ ጀምር፤ ከዚያም ቀስ በቀስ የምታነበውን መጠን እየጨመርክ ሂድ። በምታነበው ነገር ላይ ትኩረት ለማድረግ እንዲረዳህ ድምፅ እያወጣህ አንብብ።

  • በማነበው ነገር ላይ የማስብበትና የማሰላስልበት በቂ ጊዜ እንዳገኝ ምን ማስተካከያዎች ማድረግ እችላለሁ?

ጠቃሚ ምክር፦ ለጥናት ከመደብከው ጊዜ ላይ የመጨረሻዎቹን አሥር ደቂቃዎች ያነበብከውን ነገር ለመከለስ ተጠቀምባቸው።

  • በአንድ ጊዜ የተለያዩ ነገሮችን ለማድረግ የምፈተነው በምን ዓይነት ሁኔታዎች ሥር ነው?

  • በአንድ ጊዜ አንድ ነገር ላይ ብቻ ለማተኮር የትኞቹን ማስተካከያዎች ማድረግ እችላለሁ?

ጠቃሚ ምክር፦ በምታነብበት ጊዜ ሌላ ነገር ለማድረግ እንዳትፈተን ትኩረትህን የሚከፋፍሉ ነገሮችን ከአካባቢህ አርቅ።

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ጥበብን አግኝ፤ ማስተዋልንም አዳብር።”—ምሳሌ 4:5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ