የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g25 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
  • ተስፋ ይኑርህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተስፋ ይኑርህ
  • ንቁ!—2025
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ምንስ ያከናውናል?
  • ተስፋ የሚሰጥ ነገር ከየት ማግኘት እችላለሁ?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ብርሃን ይፈነጥቃል
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማስተዋወቂያ
  • የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለን ተስፋ ማድረግ እንችላለን?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2025
g25 ቁጥር 1 ገጽ 14-15
ሣር ላይ አረፍ ብሎ እየተዝናና ያለ አንድ ቤተሰብ ውብ የሆነውን መልክዓ ምድር አሻግሮ እየተመለከተ ነው።

የኑሮ ውድነትን መቋቋም

ተስፋ ይኑርህ

በምትኖርበት አገር የገበያ ዋጋ የሚጨምርበት መጠን ከገቢህ ጋር አልሄድ ብሎሃል? ራስህንም ሆነ ቤተሰብህን ማስተዳደር መቻልህ ያሳስብሃል? ከሆነ ነገን ስታስብ ስጋት ያድርብህ ይሆናል። ይሁንና እንዲህ ባለው ከባድ ሁኔታ ውስጥም እንኳ ተስፋ የራስህ ልታደርገው የሚገባ ውድ ነገር ነው።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ተስፋ ማድረግ ሲባል እንዲሁ ቁጭ ብሎ ጥሩ ነገር እንዲከሰት መመኘት ማለት አይደለም። ተስፋ ለሥራ እንድንነሳሳና ያለንበትን ሁኔታ በተሻለ መንገድ እንድንጠቀምበት አቅም ይሰጠናል። ለምሳሌ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች በአብዛኛው . . .

  • መንፈሰ ጠንካራ ናቸው

  • ከሁኔታዎች ጋር በቀላሉ ይላመዳሉ

  • ጥበብ የሚንጸባረቅበት የአኗኗር ዘይቤ ይከተላሉ፤ ይህም ጥሩ የጤና አጠባበቅ ልማዶችን ያካትታል

ምን ማድረግ ትችላለህ?

በመጀመሪያ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ዛሬ ላይ እንዴት እንደሚረዳህ ተማር። መጽሐፍ ቅዱስ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም የሚያስችሉ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦችን ይጠቁምሃል። እነዚህም ሆኑ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮች ሕይወትህን ለማሻሻል ማድረግ በምትችላቸው ነገሮች ላይ እንድታተኩር ይረዱሃል፤ እንዲሁም ወደፊት ለሚያጋጥሙህ ፈተናዎች ዝግጁ ያደርጉሃል።

“ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፣ ማስተዋልም ይጋርድሃል።”—ምሳሌ 2:11 የ1954 ትርጉም


ሁለተኛ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ምን እንደሚል ተማር። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ስትረዳ ይህ መጽሐፍ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የያዘውን ሐሳብ ለመመርመር መነሳሳትህ አይቀርም። ለምሳሌ፣ አምላክ “የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን” እንደሚመኝልህ ትማራለህ፤ ይህ ተስፋ እውን እንዲሆን ደግሞ አስተማማኝ መሠረት እንደጣለ ትረዳለህ። (ኤርምያስ 29:11) ይህ አስተማማኝ መሠረት የአምላክ መንግሥት ነው።

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ምንስ ያከናውናል?

የአምላክ መንግሥት ወደፊት መላዋን ምድር የሚገዛ መስተዳድር ነው። (ዳንኤል 2:44፤ ማቴዎስ 6:10) ከሰማይ ሆኖ የሚገዛው ይህ መንግሥት መከራን እንዲሁም ድህነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያስወግዳል፤ በምትኩ ሰላምና ብልጽግና እንዲሰፍን ያደርጋል። የሚከተሉት ጥቅሶች ይህን ያሳያሉ፦

“ደስተኛ ትሆናለህ፤ ደግሞም ትበለጽጋለህ።”—መዝሙር 128:2

የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች “በከንቱ አይለፉም።”—ኢሳይያስ 65:23

“በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል።”—መዝሙር 72:16

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እነዚህ ተስፋዎች እንደሚፈጸሙ አይጠራጠሩም፤ ምክንያቱም አምላክ ‘ሊዋሽ እንደማይችል’ ይተማመናሉ። (ቲቶ 1:2) ታዲያ አንተስ መጽሐፍ ቅዱስን ለምን አትመረምርም? መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ተስፋ ዛሬ ላይ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለማሸነፍ ውስጣዊ ጥንካሬ ይሰጥሃል፤ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ደግሞ ብሩህ አመለካከት እንዲኖርህ ያደርጋል።

ራማዝ።

“ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማርኩት ተስፋ ዓለም ላይ ያሉትን ችግሮች ጊዜያዊ አድርጌ እንድመለከት ረድቶኛል። ይህን ተስፋ ማሰቤ የኢኮኖሚው ሁኔታ እየተባባሰ ቢሄድም እንኳ ለመቋቋም የሚያስችለኝን ጥንካሬ ሰጥቶኛል።”—ራማዝ፣ ጆርጂያ

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

መጽሐፍ ቅዱስ የሰጠው ተስፋ እንደሚፈጸም መተማመን እንችላለን? የሚከተሉትን ቪዲዮዎች jw.org ላይ ተመልከት፦ መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ መሆኑን እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን? እና የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

አንዲት ሴት ከመጽሐፍ መደርደሪያ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ስትወስድ።
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ