የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 60
  • አቢግያና ዳዊት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አቢግያና ዳዊት
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ’ማስተዋልሽ የተባረከ ይሁን!’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • አንዲት ልባም ሴት ጥፋት እንዳይደርስ ተከላከለች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 60

ምዕራፍ 60

አቢግያና ዳዊት

ከዳዊት ጋር ለመገናኘት ወደ እርሱ እየመጣች ያለችው ቆንጆ ሴት ማን እንደሆነች ታውቃለህ? አቢግያ ትባላለች። ጥሩ የማስተዋል ችሎታ ስለነበራት ዳዊት መጥፎ ድርጊት ከመፈጸም እንዲቆጠብ አድርጋዋለች። ይሁን እንጂ ይህን ከመመርመራችን በፊት ዳዊት ምን ሁኔታ እንዳጋጠመው እንመልከት።

ዳዊት ከሳኦል ከሸሸ በኋላ በዋሻ ውስጥ ተደበቀ። ወንድሞቹና የተቀሩት ቤተሰቦቹ አብረውት ሆኑ። በጠቅላላ 400 ሰዎች ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉና ዳዊት መሪያቸው ሆነ። ከዚያም ዳዊት ወደ ሞዓብ ንጉሥ ሄደና ‘ወደፊት የሚያጋጥመኝን ሁኔታ እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ አንተ ጋር ይቆዩ’ አለው። ከዚያ በኋላ ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች በኮረብታዎች ውስጥ ተደበቁ።

ዳዊት አቢግያን ያገኛት ከዚህ በኋላ ነበር። ባልዋ ናባል ሀብታምና ትልቅ መሬት ያለው ሰው ነበር። 3, 000 በጎችና 1, 000 ፍየሎች ነበሩት። ናባል ክፉ ሰው ነበር። ሚስቱ አቢግያ በጣም ቆንጆ ነበረች። በተጨማሪም ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ የሚቻልበትን መንገድ ታውቅ ነበር። እንዲያውም አንድ ቀን ቤተሰቧን ከጥፋት አድናለች። ይህን ያደረገችው እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ለናባል ውለታ ውለውለታል። በጎቹን ከአደጋ በመጠበቅ ረድተውታል። ስለዚህ ከዕለታት አንድ ቀን ዳዊት ናባል አንድ ውለታ እንዲውልለት ለመጠየቅ አብረውት ከነበሩት ሰዎች መካከል ጥቂቶቹን ላካቸው። ዳዊት የላካቸው ሰዎች ወደ ናባል ሲደርሱ ናባልና ረዳቶቹ በጎቹን እየሸለቱ ነበር። በዚያ ቀን ድግስ ስለነበረ ናባል ብዙ ጥሩ ጥሩ ምግቦች ነበሩት። በዚህም ምክንያት ዳዊት የላካቸው ሰዎች ‘እኛ ውለታ ውለንልሃል። አንድም በግ አልሰረቅንህም፤ ከዚህ ይልቅ በጎችህን እንጠብቅልህ ነበር። እባክህ አሁን ጥቂት ምግብ ስጠን’ አሉት።

ናባል ‘እንደናንተ ላሉ ሰዎች ምግቤን አልሰጥም’ አላቸው። ክፉ ቃል ተናገራቸው፤ ስለ ዳዊትም ብዙ መጥፎ ነገር ተናገረ። ሰዎቹ ተመልሰው ይህን ሲነግሩት ዳዊት በጣም ተቆጣ። አብረውት የነበሩትን ሰዎች ‘ሰይፋችሁን ታጠቁ!’ አላቸው። ከዚያም ናባልንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሰዎች ለመግደል ጉዞ ጀመሩ።

ናባል የተናገረውን ክፉ ቃል የሰማ አንድ ከናባል ጋር የሚኖር ሰው የሆነውን ነገር ሁሉ ለአቢግያ ነገራት። ወዲያውኑ አቢግያ ምግብ አዘጋጀች። ምግቡን በአህዮች ላይ አስጫነችና ጉዞ ጀመረች። ከዳዊት ጋር ስትገናኝ ከአህያዋ ላይ ወረደችና በግምባርዋ መሬት ላይ ተደፍታ ‘እባክህ ጌታዬ ባሌን ናባልን ችላ በለው። እርሱ ሞኝ ነው፤ ሥራውም የሞኝ ሥራ ነው። ይህን ስጦታ አምጥቼልሃለሁ። እባክህ ተቀበለኝ፤ ለፈጸምነውም በደል ይቅር በለን’ አለች።

ዳዊት ‘አንቺ ጥበበኛ ሴት ነሽ። በበቀል ስሜት ናባልን ከመግደል እንድቆጠብ አድርገሽኛል። አሁን በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጂ’ አላት። ከጊዜ በኋላ ናባል ሲሞት አቢግያ የዳዊት ሚስት ሆነች።

1 ሳሙኤል 22:​1-4፤ 25:​1-43

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ