የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • my ታሪክ 77
  • ለምስሉ አልሰገዱም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለምስሉ አልሰገዱም
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክህ ማን ነው?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ለወርቁ ምስል አልሰገዱም
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • እምነታቸው ከባዱን ፈተና ተቋቋመ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
  • ‘አምላካችን ሊያድነን ይችላል’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
my ታሪክ 77

ምዕራፍ 77

ለምስሉ አልሰገዱም

እነዚህን ሦስት ወጣቶች ታስታውሳቸዋለህ? አዎ፣ መብላት የሌለባቸውን ምግብ አንበላም ያሉት የዳንኤል ጓደኞች ናቸው። ባቢሎናውያን ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ብለው ስም አውጥተውላቸዋል። አሁን ምን እያደረጉ እንዳሉ ተመልከት። እንደ ሌሎቹ ሰዎች ለዚህ ግዙፍ ምስል ያልሰገዱት ለምንድን ነው? ለምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

ይሖዋ ራሱ የጻፋቸውን አሥርቱ ትእዛዛት ተብለው የሚጠሩትን ሕጎች ታስታውሳቸዋለህ? ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያው ‘ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክ’ ይላል። ምንም እንኳ እንዲህ ማድረጉ ቀላል ነገር ባይሆንም እዚህ ላይ የምታያቸው ወጣቶች ይህን ሕግ አክብረዋል።

የባቢሎን ንጉሥ የሆነው ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ክብር እንዲሰጡ ብዙ ታላላቅ ሰዎችን ጠራ። ናቡከደነፆር ‘የመለከቶቹንና የበገናዎቹን እንዲሁም የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ድምፅ ስትሰሙ በግምባራችሁ ተደፍታችሁ ይህን የወርቅ ምስል አምልኩ። በግምባሩ ተደፍቶ ይህን ምስል ያላመለከ ሁሉ ወዲያውኑ በኃይል በሚነድ እሳት ውስጥ ይጣላል’ ብሎ ለሕዝቡ ተናገረ።

ናቡከደነፆር ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ እንዳልሰገዱ ሲሰማ በጣም ተቆጣ። ይዘው እንዲያመጧቸውም አዘዘ። ለምስሉ እንዲሰግዱ ሌላ ዕድል ሰጣቸው። ይሁን እንጂ ወጣቶቹ በይሖዋ ተማምነው ነበር። ናቡከደነፆርን ‘የምናገለግለው አምላካችን ሊያድነን ይችላል። ባያድነንም እንኳ ላቆምከው የወርቅ ምስል አንሰግድም’ አሉት።

ናቡከደነፆር ይህን ሲሰማ ከበፊቱ ይበልጥ በጣም ተናደደ። በዚያው አቅራቢያ ይነድድ የነበረውን እሳት ‘ከበፊቱ ይበልጥ ሰባት እጥፍ እንዲያነድዱት’ አዘዘ። ከዚያም በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩት በጣም ኃይለኛ የሆኑ ሰዎች ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን አስረው እሳቱ ውስጥ እንዲጥሏቸው አዘዛቸው። እሳቱ በጣም ይነድ ስለነበረ ኃይለኞቹ ሰዎች በእሳቱ ነበልባል ተቃጥለው ሞቱ። ይሁን እንጂ እሳቱ ውስጥ የተጣሉት ሦስቱ ወጣቶችስ ምን ሆኑ?

ንጉሡ ወደ እሳቱ ሲመለከት በጣም ደነገጠ። ‘ሦስት ሰዎች አስረን ወደሚነድደው እሳት ውስጥ ጥለናቸው አልነበረምን?’ ሲል ጠየቀ።

አገልጋዮቹ ‘አዎ’ ብለው መለሱለት።

‘አሁን ግን አራት ሰዎች በእሳቱ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ሲመላለሱ አያለሁ። አልታሰሩም፤ እሳቱም ምንም አልጎዳቸውም። አራተኛው ደግሞ አምላክ ይመስላል’ አለ። ንጉሡ ወደ እሳቱ ቀረበና ‘የልዑሉ አምላክ አገልጋዮች የሆናችሁት ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ከእሳቱ ውስጥ ውጡ!’ ብሎ ጮኸ።

ከእሳቱ ውስጥ ሲወጡ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ሁሉም ሰው መመልከት ችሎ ነበር። ከዚያም ንጉሡ ‘የሲድራቅ፣ የሚሳቅና የአብደናጎ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! ከራሳቸው አምላክ በቀር ለሌላ ለማንም አምላክ ባለመስገዳቸውና ባለማምለካቸው መልአኩን ልኮ አድኗቸዋል’ ሲል ተናገረ።

ይህ ለይሖዋ ታማኝነትን በማሳየት ረገድ ልንከተለው የሚገባ ጥሩ ምሳሌ አይደለምን?

ዘጸአት 20:​3፤ ዳንኤል 3:​1-30

የአንቀጾቹ ጥያቄዎች

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ