የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • rq ትምህርት 16 ገጽ 31
  • አምላክን ለማገልገል የምታደርገው ውሳኔ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን ለማገልገል የምታደርገው ውሳኔ
  • አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • ጥምቀትና ከአምላክ ጋር ያለህ ዝምድና
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ራሴን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ይኖርብኛል?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • አምላክን ለዘላለም ማገልገልን ዓላማህ አድርግ
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
ለተጨማሪ መረጃ
አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
rq ትምህርት 16 ገጽ 31

ትምህርት 16

አምላክን ለማገልገል የምታደርገው ውሳኔ

የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ምን ማድረግ ይኖርብሃል? (1, 2)

ራስህን ለአምላክ የምትወስነው እንዴት ነው? (1)

መጠመቅ የሚኖርብህ መቼ ነው? (2)

ለአምላክ ታማኝ ሆነህ ለመጽናት የሚያስችልህን ኃይል ልታገኝ የምትችለው እንዴት ነው? (3)

1. የአምላክ ወዳጅ ለመሆን ከፈለግህ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች በሚገባ ማወቅ (1 ጢሞቴዎስ 2:3, 4)፣ የተማርካቸውን ነገሮች ማመን (ዕብራውያን 11:6)፣ ስላደረግሃቸው ኃጢአቶች መጸጸት (ሥራ 17:30, 31) እና የአኗኗር መንገድህን መለወጥ (ሥራ 3:19) ይኖርብሃል። ከዚህ በኋላ ለአምላክ ያለህ ፍቅር ራስህን ለአምላክ እንድትወስን ሊገፋፋህ ይገባል። ይህ ማለት ብቻህን ሆነህ በግል ጸሎትህ የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ራስህን አሳልፈህ እንደምትሰጥ ለአምላክ ትናገራለህ ማለት ነው።​—ማቴዎስ 16:24፤ 22:37

2. ራስህን ለአምላክ ከወሰንክ በኋላ መጠመቅ ይገባሃል። (ማቴዎስ 28:19, 20) መጠመቅህ ራስህን ለይሖዋ የወሰንክ መሆንህን ሰው ሁሉ እንዲያውቅ ያደርጋል። ስለዚህ መጠመቅ የሚገባቸው አምላክን ለማገልገል ውሳኔ ማድረግ ወደሚያስችላቸው ዕድሜ የደረሱ ብቻ ናቸው። አንድ ሰው ሲጠመቅ መላ ሰውነቱ ለጥቂት ጊዜ ውኃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መስመጥ አለበት።a​—ማርቆስ 1:9, 10፤ ሥራ 8:36

3. ራስህን ከወሰንክ በኋላ ይሖዋ ይህንን የገባኸውን ቃል ጠብቀህ እንድትኖር ይፈልግብሃል። (መዝሙር 50:14፤ መክብብ 5:4, 5) ዲያብሎስ ይሖዋን ማገልገልህን እንድታቆም ለማድረግ ይሞክራል። (1 ጴጥሮስ 5:8) ይሁን እንጂ ወደ አምላክ በጸሎት ቅረብ። (ፊልጵስዩስ 4:6, 7) በየዕለቱ ቃሉን አጥና። (መዝሙር 1:1-3) ከጉባኤው ጋር ተቀራረብ። (ዕብራውያን 13:17) እነዚህን ሁሉ ካደረግህ ለአምላክ ታማኝ ሆነህ እንድትጸና የሚያስችልህን ኃይል ታገኛለህ። በዚህ መንገድ አምላክ የሚፈልግብህን ነገሮች ከዘላለም እስከ ዘላለም እያደረግህ ለመኖር ትችላለህ!

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ለጥምቀት የሚያስፈልገውን ዝግጅት ለማድረግ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን ወይም ሌላ ተመሳሳይ የሆነ በመጠበቂያ ግንብና ትራክት ማኅበር የታተመ መጽሐፍ ብታጠና ጥሩ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ