የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ie ገጽ 30-31
  • በዓይነቱ ልዩ የሆነ ተስፋ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በዓይነቱ ልዩ የሆነ ተስፋ!
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንተም ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • ታላቁን መከራ በሕይወት ማለፍ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ለዘላለም መኖር ሕልም አይደለም
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • ከሞት በኋላ ሕይወት —መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • አምላክ በሚያመጣው ሰላማዊ አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር ትችላለህ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
ለተጨማሪ መረጃ
ስንሞት ምን እንሆናለን?
ie ገጽ 30-31

በዓይነቱ ልዩ የሆነ ተስፋ!

“ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም።”​—⁠ዮሐንስ 11:​26

1. በሚልዮን የሚቆጠሩ ሙታን ከሞት በሚነሡበት ጊዜ ምን ዓይነት ሁኔታ ይጠብቃቸዋል?

በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት የሚነሱት ሰው አልባ በሆነች ምድር ላይ አይደለም። (ሥራ 24:​15) ከሞት ሲነሱ አካባቢው ሁሉ ውበት ተላብሶ ያገኙታል፤ በተጨማሪም ለእነሱ የተዘጋጀ መኖሪያ፣ ልብስና የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራል። እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያዘጋጀው ማን ነው? ምድራዊው ትንሣኤ ከመጀመሩ በፊት በአዲሱ ዓለም ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች መኖር እንዳለባቸው ግልጽ ነው። ግን እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?

2-4. “በመጨረሻው ቀን” የሚኖሩ ሰዎች በዓይነቱ ልዩ የሆነ ምን ተስፋ ይጠብቃቸዋል?

2 የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ በዚህ ሥርዓት የ“መጨረሻ ቀን” ውስጥ እንዳለን ያሳያል።a (2 ጢሞቴዎስ 3:​1) ይሖዋ አምላክ በሰው ልጆች ጉዳዮች ጣልቃ ገብቶ ክፋትን ከምድር ገጽ የሚያጠፋበት ጊዜ በጣም ቀርቧል። (መዝሙር 37:​10, 11፤ ምሳሌ 2:​21, 22) አምላክን በታማኝነት የሚያገለግሉ ሰዎች በዚያ ጊዜ ምን ይሆናሉ?

3 ይሖዋ ጻድቃንን ከክፉዎች ጋር አንድ ላይ አያጠፋም። (መዝሙር 145:​20) ፈጽሞ እንዲህ አድርጎ አያውቅም፤ ወደፊትም ምድርን ከክፋት በሚያጸዳበት ጊዜ እንዲህ አያደርግም። (ከዘፍጥረት 18:​22, 23, 26 ጋር አወዳድር።) እንዲያውም የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ማንም ሊቆጥራቸው ያልቻለ “ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ [የተውጣጡ] እጅግ ብዙ ሰዎች” “ከታላቁ መከራ” እንደመጡ ይናገራል። (ራእይ 7:​9-14) አዎ፣ እጅግ ብዙ ሰዎች ይህ ክፉ ዓለም ከሚጠፋበት ከታላቁ መከራ ተርፈው አምላክ ወደሚያመጣው አዲስ ዓለም ይገባሉ። በዚያ አዲስ ዓለም ውስጥ ታዛዥ የሆኑ የሰው ልጆች አምላክ የሰውን ዘር ከኃጢአትና ከሞት ለማላቀቅ በሚያዘጋጀው ግሩም ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መጠቀም ይችላሉ። (ራእይ 22:​1, 2) በመሆኑም “እጅግ ብዙ ሰዎች” ሞትን መቅመስ አያስፈልጋቸውም። እንዴት ያለ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ተስፋ ነው!

4 በዚህ አስደናቂ ተስፋ ሙሉ በሙሉ መተማመን እንችላለንን? እንዴታ! ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሰዎች ሞትን ሳይቀምሱ የሚኖሩበት ጊዜ እንደሚመጣ አመልክቷል። ኢየሱስ ወዳጁን አልዓዛርን ከሞት ከማስነሳቱ ከጥቂት ጊዜ በፊት ማርታን “ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም” ብሏት ነበር።​—⁠ዮሐንስ 11:​26

አንተም ለዘላለም መኖር ትችላለህ

5, 6. ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም መኖር ከፈለግህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

5 ገነት በሆነች ምድር ላይ ለዘላለም መኖር ትፈልጋለህን? በሞት የተለዩህን የምትወዳቸውን ሰዎች ዳግመኛ ለማግኘት ትጓጓለህን? እንግዲያው ስለ አምላክ ፈቃድና ዓላማ ትክክለኛ እውቀት ማግኘት አለብህ። ኢየሱስ ወደ አምላክ ሲጸልይ እንዲህ ብሏል:- “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”​—⁠ዮሐንስ 17:​3

6 “ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲድኑና የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ” የአምላክ ፈቃድ ነው። (1 ጢሞቴዎስ 2:​3, 4 NW) በአሁኑ ጊዜ የአምላክን ፈቃድ እያደረጉ ካሉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም መኖር የምትችለው እንዴት እንደሆነ የምትማርበት ጊዜ አሁን ነው። የይሖዋ ምሥክሮች ስለ አምላክና አምላክ እንድናሟላቸው ስለሚፈልግብን ብቃቶች ይበልጥ እንድታውቅ ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው። በአቅራቢያህ ወደሚገኝ የመንግሥት አዳራሽ ሄደህ ለምን አታነጋግራቸውም? አለዚያም ደግሞ በሚቀጥለው ገጽ ላይ ከተዘረዘሩት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መጻፍ ትችላለህ።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ተመልከት።

[ገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

“እጅግ ብዙ ሰዎች” ፈጽሞ ሞትን መቅመስ አያስፈልጋቸውም

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ