የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 5 ገጽ 8-9
  • የአምላክ ወዳጆች በገነት ውስጥ ይኖራሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ ወዳጆች በገነት ውስጥ ይኖራሉ
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የተሻለ ሕይወት እንደሚመጣ ተስፋ ተሰጥቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ገነት
    ንቁ!—2013
  • “ገነት ውስጥ እንገናኝ!”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ከአርማጌዶን በኋላ ምድር ገነት ትሆናለች
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 5 ገጽ 8-9

ትምህርት 5

የአምላክ ወዳጆች በገነት ውስጥ ይኖራሉ

ገነት አሁን ከምንኖርበት ዓለም ፈጽሞ የተለየች ናት። አምላክ ምድር በመከራና በሐዘን፣ በህመምና በሥቃይ እንድትሞላ ፈጽሞ አይፈልግም ነበር። አምላክ ወደፊት ምድርን ገነት ያደርጋታል። ገነት ምን ትመስል ይሆን? እስቲ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንመልከት:-

ሰዎች በገነት ውስጥ ሰብሰብ ብለው አስደሳች ጊዜ ሲያሳልፉ

ጥሩ ሰዎች። ገነት የአምላክ ወዳጆች መኖሪያ ትሆናለች። አንዳቸው ለሌላው መልካም ነገሮችን ያደርጋሉ። አምላክ ካወጣቸው የጽድቅ መንገዶች ጋር ተስማምተው ይኖራሉ።—ምሳሌ 2:21

የተትረፈረፈ ምግብ። በገነት ውስጥ ረሃብ አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ “በምድሩ ላይ በቂ [“የተትረፈረፈ፣” NW] ምግብ ይኑር” በማለት ይናገራል።—መዝሙር 72:16 የ1980 ትርጉም

በገነት ውስጥ የተወሰኑ ሰዎች ቤት ሲሠሩ፣ አንዳንዶች አትክልትና ፍራፍሬ ሲሰበስቡ እንዲሁም አንዲት እናት ልጇን አቅፋ

ጥሩ ቤቶችና አስደሳች ሥራ። ገነት በምትሆነው ምድር ላይ እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ ቤት ይኖረዋል። እያንዳንዱ ሰው በሚሠራው ሥራ እውነተኛ ደስታ ያገኛል።—ኢሳይያስ 65:21-23

ዓለም አቀፍ ሰላም። እርስ በርሳቸው የሚዋጉና በጦርነት የሚሞቱ ሰዎች አይኖሩም። የአምላክ ቃል “[እግዚአብሔር] ጦርነትንም ይቆርጣል” በማለት ይናገራል።—መዝሙር 46:8, 9

ጥሩ ጤና። መጽሐፍ ቅዱስ “በዚያም [በገነት ውስጥ] የሚቀመጥ:- ታምሜአለሁ አይልም” በማለት ተስፋ ይሰጣል። (ኢሳይያስ 33:24) በተጨማሪም ሽባ ወይም ዓይነ ሥውር ወይም መስማት የተሳነው ወይም መናገር የማይችል ሰው አይኖርም።—ኢሳይያስ 35:5, 6

ሥቃይ፣ ሐዘንና ሞት ያከትማሉ። የአምላክ ቃል “ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና” በማለት ይናገራል።—ራእይ 21:4

መጥፎ ሰዎች ድምጥማጣቸው ይጠፋል። ይሖዋ “ኀጥአን ግን ከምድር ይጠፋሉ፣ ዓመፀኞችም ከእርስዋ ይነጠቃሉ” በማለት ቃል ይገባል።—ምሳሌ 2:22

ሰዎች እርስ በርሳቸው ተዋድደውና ተከባብረው ይኖራሉ። የፍትሕ መጓደል፣ ጭቆና፣ ስግብግብነትና ጥላቻ አይኖርም። ሰዎች አንድ ሆነው አምላክ ካወጣቸው የጽድቅ መንገዶች ጋር ተስማምተው ይኖራሉ።—ኢሳይያስ 26:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ