የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • kp ገጽ 16-19
  • አምላክ ቃል የገባው አዲስ ዓለም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ቃል የገባው አዲስ ዓለም
  • ነቅተህ ጠብቅ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘የአዲስ ሰማይና የአዲስ ምድር’ አጀማመር
    በሕይወት ተርፎ ወደ አዲስ ምድር መግባት
  • በትንቢት እንደተነገረው ሁሉን አዲስ ማድረግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ከአርማጌዶን በኋላ ምድር ገነት ትሆናለች
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት
    ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
ነቅተህ ጠብቅ!
kp ገጽ 16-19

አምላክ ቃል የገባው አዲስ ዓለም

በጽሑፍ የሰፈረው የአምላክ ቃል ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ የሰጠውን ተስፋ ሲገልጽ “ጽድቅ የሚኖርበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በተስፋ ቃሉ መሠረት እንጠባበቃለን” ይላል።—2 ጴጥሮስ 3:13

“አዲስ ሰማይ” የተባለው ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ሰማይን ከአገዛዝ ጋር አያይዞ ይገልጸዋል። (የሐዋርያት ሥራ 7:49) ይህ “አዲስ ሰማይ” ምድርን የሚገዛ አዲስ መንግሥት ነው። አዲስ የተባለው አሁን ያለውን የአገዛዝ ሥርዓት ስለሚተካ ነው፤ በተጨማሪም ይህ መንግሥት የአምላክን ዓላማ ደረጃ በደረጃ ለማስፈጸም የተወሰደ አዲስ እርምጃ ነው። ኢየሱስ እንድንጸልይ ያስተማረውም ስለዚህ መንግሥት ነው። (ማቴዎስ 6:10) ይህን መንግሥት ያቋቋመው ይሖዋ በመሆኑና ይሖዋ ደግሞ የሚኖረው በሰማይ ስለሆነ ይህ መንግሥት “መንግሥተ ሰማይ” ተብሎ ተጠርቷል።—ማቴዎስ 7:21

“አዲስ ምድር” የተባለውስ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ምድር ዘላለማዊ መኖሪያ እንደሆነች በግልጽ ስለሚናገር ሌላ ግዑዝ ምድር ይፈጠራል ማለት አይደለም። “አዲስ ምድር” የሚለው አነጋገር አዲስ ሰብዓዊ ኅብረተሰብን ያመለክታል። ክፉዎች ከምድር ገጽ ተጠራርገው ስለሚጠፉ ምድር አዲስ ትሆናለች። (ምሳሌ 2:21, 22) በዚያን ጊዜ በምድር ላይ የሚኖሩ ሁሉ ፈጣሪን የሚያከብሩና የሚታዘዙ ከመሆኑም በላይ ካወጣቸው መሥፈርቶች ጋር ተስማምተው ይኖራሉ። (መዝሙር 22:27) የሁሉም ብሔራት ሕዝቦች እነዚህን መሥፈርቶች እንዲማሩና አሁኑኑ ሕይወታቸውን ከእነዚህ መሥፈርቶች ጋር እንዲያስማሙ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው። አንተ ይህን እያደረግክ ነው?

አምላክ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ ሁሉም ሰው ለይሖዋ ሥልጣን ተገዥ ይሆናል። ለአምላክ ያለህ ፍቅር እንድትታዘዘው ይገፋፋሃል? (1 ዮሐንስ 5:3) በቤት፣ በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት ወይም በሌላ በማንኛውም የሕይወትህ ዘርፍ ይሖዋን እንደምትታዘዝ ታሳያለህ?

በዚህ አዲስ ዓለም ውስጥ መላው የሰው ዘር እውነተኛውን አምላክ አንድ ሆኖ ያመልካል። የምታመልከው የሰማይንና የምድርን ፈጣሪ ነው? ይህ አምልኮህ ከሁሉም ብሔራት፣ ዘርና ቋንቋ ከተውጣጡ እውነተኛ አምላኪዎች ጋር አንድ አድርጎሃል?—መዝሙር 86:9, 10፤ ኢሳይያስ 2:2–4፤ ሶፎንያስ 3:9

[በገጽ 17 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ይህን ተስፋ የሰጠው አምላክ

ይህን ተስፋ የሰጠው አምላክ የግዑዙ ሰማይና የፕላኔቷ ምድር ፈጣሪ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነተኛ አምላክ” ሲል ጠርቶታል።—ዮሐንስ 17:3

አብዛኞቹ የሰው ልጆች ራሳቸው የሠሯቸውን አማልክት ያመልካሉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በድን በሆኑ ምስሎች ፊት ይሰግዳሉ። ሌሎች ደግሞ ሰብዓዊ ተቋማትን፣ ቁሳዊ ሀብትን፣ ፍልስፍናን ወይም የራሳቸውን ምኞት እንደ ጣዖት ያመልካሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ እናምናለን የሚሉ አንዳንድ ሰዎችም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ “እውነተኛ አምላክ” ሲል የሚጠራውን ፈጣሪ ስም ያቃልላሉ።—ዘዳግም 4:35 NW

ፈጣሪ ራሱን አስመልክቶ ሲናገር “እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ስሜም ይህ ነው” ብሏል። (ኢሳይያስ 42:5, 8 NW) ይህ ስም በመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ 7,000 ጊዜ ያህል ተጠቅሶ ይገኛል። ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮቹ “በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ” ብለው እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል።—ማቴዎስ 6:9

እውነተኛው አምላክ ምን ባሕርያት አሉት? ይሖዋ ‘ሩኅሩኅ፣ ቸር፣ ለቁጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ’ እንደሆነና ሆን ብለው ትእዛዙን የሚተላለፉትን ሰዎች ሳይቀጣ እንደማያልፍ ገልጿል። (ዘፀአት 34:6, 7) ባለፉት የታሪክ ዘመናት ከሰው ልጆች ጋር በነበረው ግንኙነት ይህ መግለጫ እውነት መሆኑ በግልጽ ታይቷል።

ስሙም ሆነ የዚህ ስም ባለቤት የሆነው አምላክ እንደ ቅዱስ ሊታዩ ይገባል። ይሖዋ ፈጣሪና የጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ በመሆኑ ልንታዘዘውና ልናመልከው ይገባል። ታዲያ አንተ ይህን እያደረግክ ነው?

[በገጽ  18 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]

በመጪዎቹ “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” የሚከናወኑት ለውጦች ምንድን ናቸው?

ምድር ወደ ገነትነት ትለወጣለች ሉቃስ 23:43

ከሁሉም ብሔር፣ ዘርና ቋንቋ የተውጣጣና በፍቅር የተሳሰረ ዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ይኖራል ዮሐንስ 13:35፤ ራእይ 7:9,10

ዓለም አቀፍ ሰላምና ፀጥታ ይሰፍናል መዝሙር 37:10,11፤ ሚክያስ 4:3,4

አርኪ ሥራና የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራል ኢሳይያስ 25:6፤ 65:17, 21-23

በሽታ፣ ሐዘንና ሞት ይጠፋል ኢሳይያስ 25:8፤ ራእይ 21:1,4

መላው የሰው ዘር እውነተኛውን አምላክ አንድ ሆኖ ያመልካል ራእይ 15:3,4

[በገጽ 19 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]

ከዚህ በረከት ተካፋይ ትሆናለህ?

አምላክ ሊዋሽ አይችልም!—ቲቶ 1:2

ይሖዋ “ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል” ሲል ተናግሯል።—ኢሳይያስ 55:11

በአሁኑ ጊዜ ይሖዋ “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” በመፍጠር ላይ ነው። በሰማይ የተቋቋመው መንግሥት ሥራውን ጀምሯል። ‘የአዲሱ ምድር’ መሠረትም ተጥሏል።

የራእይ መጽሐፍ ‘አዲሱ ሰማይና አዲሱ ምድር’ የሚያስገኟቸውን አስደናቂ በረከቶች ከዘረዘረ በኋላ የጽንፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ የሆነው አምላክ “እነሆ፤ እኔ ሁሉን ነገር አዲስ አደርጋለሁ” ሲል እንደተናገረ ይገልጻል። በተጨማሪም አምላክ “ይህ ቃል የታመነና እውነት ስለ ሆነ ጻፍ” ሲል ተናግሯል።—ራእይ 21:1, 5

አሁን ትልቁ ጥያቄ ‘በአዲሱ ሰማይ’ የሚተዳደረው “አዲስ ምድር” አባል ለመሆን በግለሰብ ደረጃ አስፈላጊውን ማስተካከያ እያደረግን ነው? የሚለው ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ