ክፍል 8
መዝናኛ
እንደ ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ቴሌቪዥንና የኤሌክትሮኒክ ጨዋታዎች ያሉትን መዝናኛዎች ምን ያህል ታዘወትራለህ?
□ አልፎ አልፎ
□ በቀን አንዴ
□ በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ
በመዝናኛ ምርጫህ ረገድ ትልቁን ሚና የሚጫወተው ማን ወይም ምንድን ነው?
□ እኩዮችህ
□ ወላጆችህ
□ ማስታወቂያ
የእናንተ ትውልድ ከቀድሞዎቹ ትውልዶች ሁሉ ይልቅ በመዝናኛ ረገድ ብዙ ምርጫ እንዳለው የታወቀ ነው። ይሁንና በቀን ውስጥ ያለህ ጊዜ 24 ሰዓት ብቻ ነው። ከዚህም ሌላ የምትመርጠው መዝናኛ በአስተሳሰብህና በዝንባሌህ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። ታዲያ ለመዝናኛ የምታውለው ጊዜ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ምን ማድረግ ትችላለህ? የመዝናኛውን ዓይነት መምረጥ የምትችለው እንዴት ነው? ከ30-33 ያሉት ምዕራፎች ስለ መዝናኛ ምርጫህ በቁም ነገር እንድታስብ ይረዱሃል።
[በገጽ 244 እና 245 ላይ የሚገኝ ባለሙሉ ገጽ ሥዕል]