መዝሙር 82
እንደ ክርስቶስ ገር መሆን
በወረቀት የሚታተመው
1. ከሁሉ ’ሚበልጥ ሰው ነበር ክርስቶስ፤
ኩራት፣ በምኞት የማይወቀስ።
ባምላክ ዓላማ ውስጥ ልዩ ቦታ ’ለው፤
ያም ሆኖ ምንጊዜም ልቡ ትሑት ነው።
2. ቀርቧል ግብዣው ሸክም ለከበዳችሁ፤
ልዝብ ቀንበሩን ሊሸከም አብሯችሁ።
መንግሥቱን ማስቀደም እረፍት ያስገኛል፤
ጌታችን ገር ነው፤ ትሑት ሰው ይወዳል።
3. ጌታ “ወንድማማች ናችሁ” ብሎናል፤
ለመብለጥ ሳይሆን እንጣር ለማገልገል።
ገሮችና ትሑታን ዋጋ ’ላቸው፤
አምላክ ቃል ገብቷል ምድርን ሊያወርሳቸው።