መዝሙር 67
በየዕለቱ ወደ ይሖዋ መጸለይ
በወረቀት የሚታተመው
1. ወዳምላክ ጸልይ፤ ጸሎት ሰሚ ነው።
ይሖዋ የሰጠን ታላቅ መብት ነው።
እንደ ጓደኛህ ሁሉን ንገረው፤
እምነት የሚጣልበት አምላክ ነው።
በየ’ለቱ እንጸልይ።
2. እናመስግነው ሕይወት ሰጥቶናል፤
ይቅር ባይ ከሆን ይቅር ይለናል።
ላምላክ ’ንናዘዝ በደላችንን፤
አፈር እንደሆን ያውቃል ፈጥሮናል።
በየ’ለቱ እንጸልይ።
3. በችግር ጊዜ ወደሱ ’ንጸልይ፤
አባታችን ነው ከኛ ’ማይለይ።
እንዲጠብቀን እንማጸነው፤
አይፈራም የሚታመንበት ሰው።
በየ’ለቱ እንጸልይ።
(በተጨማሪም ማቴ. 6:9-13፤ 26:41ን እና ሉቃስ 18:1ን ተመልከት።)