መዝሙር 59
ራሳችንን ለአምላክ ወስነናል!
በወረቀት የሚታተመው
1. የሰማዩ አባት ወደ ልጁ ሳበን፤
የ’የሱስ ተከታዮች ሆንን።
ከአምላክ ታላቅ ዙፋን፣
ፈንጥቋል የ’ውነት ብርሃን።
እምነታችን ጠንክሯል፤
ራሳችንንም ክደናል።
(አዝማች)
ወደን ላምላክ ራሳችንን ወስነናል፤
ንብረቱ መሆን ደስታ ይሰጣል።
2. አምላካችንን ዘላለም ለማገልገል፣
በጸሎት ለሱ ቃል ገብተናል።
ወደር የለውም ደስታው፣
ውስጣዊ እርካታ ’ለው፣
ምሥራቹን ስንሰብክ፣
በሱ ስምም ስንታወቅ።
(አዝማች)
ወደን ላምላክ ራሳችንን ወስነናል፤
ንብረቱ መሆን ደስታ ይሰጣል።