መዝሙር 64
እውነትን የራስህ አድርግ
በወረቀት የሚታተመው
1. የእውነት መንገድ በጣም ግሩም ሕይወት ነው፤
መምረጥ ግን የራስህ ፋንታ ነው።
ስለዚህ ስማ ይሖዋ ’ምላክ ሲመክርህ፤
በሱ ላይ እምነት ይኑርህ።
(አዝማች)
እውነት የራስህ፣
ይሁን ለአንተ ሕያው።
ያኔ ይሖዋ ይባርክሃል፤
ደስታህም ይጨምራል።
2. ይሖዋንና መንግሥቱን ለማስቀደም
ጊዜና ጥረት ቢጠይቅም፣
ባዲሱ ዓለም ደስታና አርኪ ሕይወት
ይኖርሃል ለዘላለም።
(አዝማች)
እውነት የራስህ፣
ይሁን ለአንተ ሕያው።
ያኔ ይሖዋ ይባርክሃል፤
ደስታህም ይጨምራል።
3. በይሖዋ ዘንድ ሁላችንም ልጆች ነን፤
የሱን መመሪያ እንሻለን።
ከይሖዋ ጋር ሁሌም አብረን ከሄድን
በረከቱን እናጭዳለን።
(አዝማች)
እውነት የራስህ፣
ይሁን ለአንተ ሕያው።
ያኔ ይሖዋ ይባርክሃል፤
ደስታህም ይጨምራል።
(በተጨማሪም መዝ. 26:3ን፣ ምሳሌ 8:35፤ 15:31ን እና ዮሐ. 8:31, 32ን ተመልከት።)