መዝሙር 85
ከይሖዋ የምናገኘው ሙሉ ሽልማት
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ ታማኝ የሆነ አምላክ ነው፤
ከልብ ’ሚያመልኩትን ያውቃል።
ታማኝነት ብዙ ነገር ሊያሳጣ እንደሚችልም ይረዳል።
ቤተሰብን፣ ወዳጆችን ብታጣም፣
አምላክ ይሄን ሁሉ ያውቃል።
አሁን ወንድሞችና እህቶችን፣
ከዚያም ሕይወት ይሰጥሃል።
(አዝማች)
የመጽናናት አምላክ ሁሉን አይቶ፣
ወሮታውን ይክፈልህ አሟልቶ።
በክንፎቹ ሥር ይከልልህ።
ይሖዋ ታማኝ ነው፤ አይዋሽም ከቶ።
2. አንዳንዶች በምርጫ ወይ ባጋጣሚ፣
ሳያገቡ ይኖራሉ።
ታማኝ ሆነው መንግሥቱን ካስቀደሙ፣
በረከቱን ያገኛሉ።
ብቸኝነት ሊሰማቸው ይችላል፣
ነጠላ በመሆናቸው።
ታማኝ ወንድም፣ እህቶቻችን ናቸው፤
ድጋፍ፣ ፍቅር እንስጣቸው።
(አዝማች)
የመጽናናት አምላክ ሁሉን አይቶ፣
ወሮታውን ይክፈልህ አሟልቶ።
በክንፎቹ ሥር ይከልልህ።
ይሖዋ ታማኝ ነው፤ አይዋሽም ከቶ።
(በተጨማሪም መሳ. 11:38-40ን፣ ሩት 2:12ን እና ማቴ. 19:12ን ተመልከት።)